ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የሐዋሳ ዙሪያ የሶላር መስኖ ፖምፕ ፕሮጀክት የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ አይነተኛ ሚና እንዳለው ገለጹ።
ሚያዚያ 26/2017ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በቅርቡ ተመርቆ ለአገልግሎት የበቃውን የሐዋሳ ዙሪያ የሶላር የመስኖ ፖምፕ ፕሮጀክት የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ አይነተኛ ሚና አለው ብለዋል።
ፕሮጀክቱ 150 ሄክታር መሬት በመስኖ የሚያለማ ሲሆን 300 ቤተሰቦችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ተናግረዋል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከሲዳማ ክልልና ከዩኤን ዲፒ ጋር በመተባበር የተገነባው
ፕሮጀክቱ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።
በነገው እለት ተሳታፊዎቹ የሶላር መስኖ ፓምፕ ፕሮጀክቱን የሚጎበኙ መሆኑን የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የጉብኝቱ ዋና አላማም ተሞክሮውን ወደ የክልላቸው በመውሰድ እንዲተገብሩና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ነው ብለዋል።
ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊን ጨምሮ የሲዳማ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ኢ/ር ከበደ ጋኖሌ፣ የኦሮሚያ ፣ ደቡብና ማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስራ ሀላፊዎች በፕሮጀክቱ የለሙ የመስኖ ማሳዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።