የውሃ ሀብት ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም ውሃን ማእከል ያደረገ የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት የቤዝን እቅድ መተግበር እንደሚገባ ተጠቆመ።

የውሃ ሀብት ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም ውሃን ማእከል ያደረገ የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት የቤዝን እቅድ መተግበር እንደሚገባ ተጠቆመ። መጋቢት 07/2017 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ)በዋቢሸበሌ ቤዝን የሚተገበረው የቤዚን አቀፍ ዘላቂነት ማረጋገጫ ፕሮጀክት (BaSIRNET ማስጀመሪያ መርግብር በተካሄደበት ወቅት የውሃ ሀብት ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም ውሃን ማእከል ያደረገ የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት የቤዝን እቅድ መተግበር እንደሚገባ ተጠቆመ። የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ ውሃን ማዕከል ያደረገ የተቀናጀ ባለድርሻ አካላት የቤዚን እቅድ፣ የተፋሰስና የውሃ አካላት ጥበቃ፣ አሳታፊና ፍትሃዊ የውሃ ሀብት ምደባና አጠቃቀም ፈቃድ ስርዓት፣ ዘመናዊ የመረጃ ስርዓት፣ ውጤታማ የባለድርሻ አካላት ትስስር መፍጠርን በውሃ ሀብታችን ዙሪያ የሚታዩትን ተግዳሮቶች እልባት ለመስጠት ወሳኝ ናቸው ብለዋል። የማስጀመሪያ መርሃግብሩ ላይ የኢትዮጵያ የውሃ ሀብት አስተዳደር አሁናዊ ሁኔታ ላይ፤ የብሔራዊ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ፕሮግራም ምንነትና አተገባበር ላይ፤ እንዲሁም የቤዚን አቀፍ ዘላቂነት ማረጋገጫ ፕሮጀክት (BaSIRNET) ምንነትና አተገባበር ለይ ለውይይት መነሻ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን፤ ከሶማሌ ብሔራዊ ክልል እና ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ከተለያዩ ቢሮዎች በመጡ ተሳታፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ውይይት ተደርጎባቸዋል። በውይይቱ ወቅት ለቤዚን አቀፍ ዘላቂነት ማረጋገጫ ፕሮጀክት ውጤታማነት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ አስፈለጊ መሆኑ ተጠቁሟል።

Share this Post