ባለፋት ዘጠኝ ወራት ያስመዘገብናቸው ድሎች ሁሉ በዘርፋ ያሉ ችግሮችን እንደሚቀንሱ ተገለጸ፡፡
መጋቢት 7/2017ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2017ዓ.ም የበጀት ዓመት የ9ወራት እቅድ አፈጻጸምን ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ገምግሟል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በጋራ በመሆን በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ በውይይት ለተነሱ ጥያቄዎች፣ ሀሳብና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው ባለፋት ዘጠኝ ወራት ያስመዘገብናቸው ድሎች ሁሉ በዘርፋ ያሉ ችግሮችንም እንደሚቀንሱ ጠቁመዋል።
በመድረኩ በዘጠኝ ወር እቅድ አፈጻጸም የትኩረት ማዕከል የሆኑ ዋና ዋና ተግባራት ፣ የተገኙ ውጤቶች፣የታዩ ክፍተቶች እና የትኩረት አቅጣጫዎች በተለይ የሲቪል ሰርቫንቱ ሪፎርም በማድረግ ስራና ሰራተኛውን በማገናኘት ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያገኘሁትን መልካም ተሞክሮ በመቀመር በተሰማራሁበት ዘርፍ ላይ ለመተግበር የተማርኩበት መድረክ ነው ብለዋል።
በመጨረሻም በቀጣይ የተቋሙን የመፈፀም አቅም ለማሻሻል ሁሉም ፈፃሚ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ በማሳሰብ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡