ክቡር ሚኒስትሩ ከአፍሪካ ግሪን ሀይድሮጅን ፓርትነርሺፕ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ ከአፍሪካ ግሪን ሀይድሮጅን ፓርትነርሺፕ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡ ሚያዝያ 02/2017 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ከአፍሪካ ግሪን ሀይድሮጅን ፓርትነርሺፕ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በኢትዮጵያ ግሪን ሀይድሮጅን ላይ ለመስራት አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸውን አንስተው፤ የአፍሪካ ግሪን ሀድሮጅን ፓርትነርሽፕ ለሚያደርጋቸው ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡ የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ በበኩላቸው በግሪን ኢነርጂ ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የመንግስትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ማእቀፍን መተግበር እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ የግሪን ሀይድሮጅን ፓርትነርሽፕ አመራሮች በበኩላቸው ፓርትነርሽፑ ከንግድ ድርጅቶች፣ ከአካዳሚ ዘርፍ፣ ከአልሚዎች የተውጣጡ 45 አባላት ያሉት ስብስብ መሆኑን ጠቁመው ዘርፉን ለማበረታታት የተቋቋመ ስብስብ መሆኑን ገልጸዋል። በአፍሪካ አረንጓዴ እና የተፈጥሮ ሃይድሮጅን ላይ የሚመክር አለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል (African Green and Natural Hydrogen Conference) መካሄዱ ይታወቃል፡፡

Share this Post