የሚታዩ ክፍተቶች ቀጣይነት ባለው አቅም ግንባታ ስራ በመፍታት ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
መጋቢት 26/2017 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የብሔራዊ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም አካል የሆነው የአደሌ ፕሮጀክት አተገባበር እየተሰጠ ባለው ስልጠና ላይ የሚታዩ ክፍተቶች ቀጣይነት ባለው አቅም ግንባታ ስራ በመፍታት ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
በአደሌ ፕሮጀክት አተገባበር ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ላይ በቀረበው ሰነድ ላይ በተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚነስትር ዲኤታ ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ በሰጡት ማጠቃለያ ላይ የሚታዩ ክፍተቶች ቀጣይነት ባለው አቅም ግንባታ ስራ በመፍታት ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት በመስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊና በኦሮሚያ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ የኢነርጂ ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሶሬሳ በበኩላቸው እንደ ሀገር ከፍተኛ የሆነ የታዳሽ ሀይል ቢኖርም ጥቅም ላይ የዋለው አነስተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከፍተኛ የሀይል ችግር አለበት ሆኖም ችግሩን ለመቅረፍና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡
አቶ ተስፋዬ በማከል አሁን ላይ ከዋና መስመር ውጭ ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ታቅዶ በአደሌ ፕሮጀክት የሶላር ሀይል እየተሰራ ሲሆን ይህንን ፕሮጀክት ሲተገበር ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት የአቅም ግንባታ ስልጠና መሠጠቱ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል ።
አቶ ተስፋዬ በማያያዝ ኤሌክትሪክ ሀይል ተደራሽ ለማድረግ ሁሉም ክልል የታዳሽ ሀይል ላይ በትኩረት መሰራት እንዳለበትም አሳስበዋል።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኤሌክትርፍኬሽን እና የኢነርጂ መረጃ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ዳቢ ፕሮጀክቱ በዋናነት የክልሎችና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎን የሚጠይቅና የሚተገበር መሆኑን አውስተው፤ ስልጠናውም በአደሌ ፕሮጀክት የአካባቢና ማሕበራዊ አስተዳደር መተግበሪያ ሰነዶች ላይ ሰፊ ትኩረት በማድረግ እንደተሠጠ አብራርተዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ አደሌ ፕሮጀክት ከስርዓተ ጾታ ጋር በተለይ ለሴቶች ዘመናዊ ኢነርጂን ተደራሽ በማድረግ ያለባቸውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና የጤና ችግሮችን ለመፍታት በሚሠጠው ጠቀሜታ ላይ የአደሌ ፕሮጀክት ጀንደር ስፔሻሊስ የሆኑት ወ/ሮ አምሳሉ ሁንዴ ገለጻ አድርገዋል።