የምስራቅ ድል አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዲጅታል ኤግዚቢሽን ማዕከልን ጎበኙ፡፡

የምስራቅ ድል አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዲጅታል ኤግዚቢሽን ማዕከልን ጎበኙ፡፡ መጋቢት 25/2017ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) አዲስ አበባ የምስራቅ ድል አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዲጅታል ኤግዚቢሽን ማዕከልን ጎበኙ፡፡ በማዕከሉ በነበራቸው ቆይታ እንደ ሀገር ያለንን የከርሰምድርና የገጸ ምድር የውሃ ሀብት አጠቃቀም ፣ አያያዝ እና ህዳሴ ግድብን በሚመለከት በባለሙያ በስፋት ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን በተለይም ከህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ከተማሪዎቹ ለተነሱ በርካታ ጥያቄዎች ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የምስራቅ ድል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ር/መምህር የሆኑት አቶ ገነነ ደጀኔ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቴክኖሎጅን ተጠቅሞ ስለውሃ ሀብታችን አጠቃቀም፣ አያያዝና አጠቃላይ መረጃ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን ግንዛቤ እንድንወስድ መደረጉ በእጅጉ የሚመሰገን ነው ብለዋል፡፡ ሌሎች ጎረቤት ሀገራት በአባይ ተፋሰስ የተሻለ ግንዛቤ ኖሯቸው የሚያነሱትን የግል ተጠቃሚነት ጥያቄ የሚመልስ ትውልድ ለማፍራትም የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ስራ ነው ብለዋል፡፡ እንደ ትምህረት ተቋምም ባገኘነው ግንዛቤ መሰረት ለተማሪዎች፣ መምህራን ወላጅና አጠቃላይ ለትምህረት ቤት ማህበረሰቡ የባለቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው የማስረዳት አቅም ለመፍጠር እንሰራን ብለዋል፡፡ የምስራቅ ድል ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሀናን ሙሃመድ አባይ ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይና ወደ እድገት ጎዳና ለምታደርገው ጉዞ ትልቅ ማሳያ ነው ብላለች፡፡ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀምም ስለ አባይ ተፋሰስ በአጠቃላይ ስለ ኢትዮጵያ የውሃ ሀብት በሚገባ መሰራት አለበትም ትላለች ተማሪ ሀናን ፡፡ በጉብኝቱ የትምህርት ቤቱ ከአምስተኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች እና አንዳንድ መምህራን ተሳትፈዋል፡፡

Share this Post