በአለም ባንክ ልዑካን ቡድን የመስክ ጉብኝት ተካሄደ።

በአለም ባንክ ልዑካን ቡድን የመስክ ጉብኝት ተካሄደ። መጋቢት 24/2025 (ው.ኢ.ሚ) የአለም ባንክ ልዑካን ቡድን ከኢትዮጲያ ጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት አስተባበሪዎች ጋር በመሆን በ2016 በጀት ዓመት በታችኛው አዋሽ ተፋሰስ በአይሰኢታ እና አፋምቦ ወረዳዎች ላይ የተሰሩ የጎርፍ መከላከል ስራዎች ላይ የመስክ ጉብኝት አደረጉ። ልዑካን ቡድኑ ሰመራ ሲገቡ በኢሊ ሚራህ አየር ማረፊያ በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በጉብኝቱ ላይ ከአፋር ክልል ክቡር አቶ ዑመር ኑር አርባ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንትና የመሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ወላኣ ዊቲካ የመስኖና ተፋሰስ ቢሮ ሃላፊ እና ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች እንዲሁም የአዋሽ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አደን አብዶ እና የሁለቱም ወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል። በጉብኝቱም ወቅት በባለፈው ክረምት የተሰሩ የቅድመ ጎርፍ መከላከል ስራዎች በኢትዮጵያ ጎርፍ መከላከል ቴክኒክ ቡድን ገለጻ የተደረገ ሲሆን የዓለም ባንክ ቡድኑም ቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ላይ ግብዐቶችን እና ግብረ-መልስ ተሰጥቷል፡፡ በሁለቱም ወረዳዎች ላይ የሚገኙ ማህበረሰብ ለአለም ባንክ ቡድኑ ከፍተኛ አቀባበል ካደረጉላቸው በኃላ የምስጋና ሽልማት አበርክቶላቸዋል። በአዋሽ ዙሪያ የተካሄደው የመስክ ምልከታ የተጠናቀቀ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም በ2017 በጀት ዓመት በስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ዙሪያ የሚሰሩ የጎርፍ መከላከል ስራዎች የመስክ ጉብኝት ይደረጋል።

Share this Post