ያሉንን በረከቶች አውጥተን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ያሉንን በረከቶች አውጥተን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ መጋቢት 23/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ "ትላንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና" በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ያሉንን በረከቶች አውጥተን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ በኢትዮጵያ የቱሪዝም ሀብት ለላቀ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መንግስት የቱሪዝም መዳረሻ ልማትና የቱሪዝም ምርቶችን ከማስፋፋት አንፃር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች 17 ቋሚ ቅርሶችን ከከፍተኛ እስከ መካከለኛ ጥገና የተደርጎላቸው ሲሆን 472 የሀገር ውስጥና የውጪ ባለሀብቶችም ዘርፉንም እንደተቀላቀሉ ክቡር ሚኒስትሩ ገልፀዋል። ከለውጡ ጋር ተያይዞ ቴክኖሎጂዎችን በማዘመን ከኢንሳ ጋር በጋራ እየተሰራ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ "ብልፅግና ሰው ተኮር ነው" የተባለው በምክንያት ነው ብለዋል። ከቢሮ ወደ ገበታ ለሸገር፣ ከገበታ ለሸገር ወደ ገበታ ለሀገር፣ ከገበታ ለሀገር ወደ ገበታ ለትውልድ በፍጥነት የተሸጋገረው የልማት ስራዎች ሁሉ የመጋቢት ፍሬዎች ሲሆኑ ባለፉት ሰባት አመታት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ የነበሩ ብልሹ አሰራርን በማስተካከል ለዛሬው ስኬታችን እንድንበቃም ዕድል ፈጥሯል ብለዋል። በኢትዮጵያ ግብርና፣ ቱሪዝምና ማዕድን ትኩረት የተሰጣቸው ዘርፎች ሲሆኑ መሬትን፣ ውሃንና የሰው ሀብትን በአግባቡ የመጠቀም ልምድን እንዲኖረን ያደረጉን የመጋቢት ፍሬዎች በድጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ በነበሩ ጥረቶች፤ ለዜጎች ምቹ ያልነበሩ የሀገራችን ከተሞች ትኩረት ተሰጥቷቸው በማዘመን የኮሪደር ልማት ፍሬዎች መሆናቸውን በቀረበው ሰነድ ተመላክቷል። በመጨረሻም እንደ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተመዘገቡ ስኬቶችን ሁሉም የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች የተሰማሩበትን ዘርፍ እንደ መጋቢት ፍሬዎች እንዲያስቀጥል አሳስበዋል። በመድረኩም "የመጋቢታውያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች" በሚል በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ከሰራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ክቡር ሚኒስትሩ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

Share this Post