በሞዮ ወረዳ የሜጢ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በሞዮ ወረዳ የሜጢ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አገልግሎት መስጠት ጀመረ። መጋቢት 17/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰምድር ፕሮጀክት አካል የሆነው በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በሞዮ ወረዳ የሚጤ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አገልግሎት መስጠት ጀመረ። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ቡድን በሜጢ ቀበሌ በመገኘት የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱን አገልግሎት አስጀምረዋል። ፕሮጀክቱ ከተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ቀድሞ አገልግሎት መስጠቱ ታውቋል። ከ75 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ የተገነባው ፕሮጀክት 2140 የቀበሌዋን ማህበረሰብ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ያደርጋል። 50 ሜትር ኪዮብ ሪዘርቬር ያለው ፕሮጀክቱ አራት ቦኖዎችና ሶስት የከብቶች እና አንድ የፍየሎች መጠጫ ገንዳ የተካተተበት ነው።

Share this Post