በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ጉጂ ዞን የፊንጫዋ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የመስክ ምልከታ ተካሄደ።
መጋቢት 16/2017 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ቡድን በምእራብ ጉጂ ዞን ፊንጫዋ ከተማ በመገኘት የፊንጫዋ ከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የደረሰበትን አፈጻጸም ገምግመዋል።
የፊንጫዋ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት አፈጻጸም 62 በመቶ በላይ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከ35 ሺህ በላይ የአካባቢውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደርጋል።
ፕሮጀክቱ ከዋን ዋሽ ፕሮግራም በተገኘ በጀት በውሃ ልማት ፈንድ ብድር የሚተገበር ነው።
በመስክ ጉብኝቱ ክቡር ሚኒስትሩን ጨምሮ የውሃ ሀብት አስተዳደር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ ፣ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፉው ዲንጋሞ ፣ የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ እንዲሁም፤ የኦሮሚ ክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።