ክቡር ሚኒትሩ ከአልጀሪያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የኢነርጂ፣ ማእድንና ታዳሽ ኢነርጂ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።

ክቡር ሚኒትሩ ከአልጀሪያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የኢነርጂ፣ ማእድንና ታዳሽ ኢነርጂ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ። መጋቢት 15/2017 ዓ.መረ. (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ከአልጀሪያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የኢነርጂ፣ ማእድንና ታዳሽ ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር መሃመድ አርካብ ጋር ተወያዩ፡፡ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በኢትዮጵያና በአልጀርያ መካከል ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳለ ጠቅሰው፤ ለዚህም በቀጠናዊ፣ በአህጉራዊ እና አለማቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የሚታየው መደጋገፍ ጥሩ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ ክቡር ሚነስትሩ ኢትዮጵያ በምሰራቅ አፍሪካ የሀይል ትስስር እንዲፈጠር በማድረግ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተች መሆኑን ጠቁመው፤ ኢነርጂ ላይ የሚሰሩ የአልጀሪያ ካምፓኒዎች በኢትዮጵያ የሀይል ልማት ዘርፍ ላይ መሳተፍ የሚችሉበት መልካም አጋጣሚ እንዳለ ተናግረዋል፡፡ ለዚህም በኢትዮጵያ በኢነርጂ ዘርፍ የሚወጡ አለምአቀፍ ጨረታዎች ላይ የአልጀርያ ድርጅቶች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የአልጀሪያ የኢነርጂ. ማእድንና ታዳሽ ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር መሃመድ አርካብ በበኩላቸው ሶኔለጋዝ (Sonelgaz) እና ሶናትራክ (Sonatrach) የመሳሰሉ በሀይል ማምረት፣ በሀይል ስርጭት እንዲሁም ለሀይል ስርጭት አስፈላጊ የሆነ ግብዓት የሚያመርቱ የአልጀሪያ ካምፓኒዎች ጨምሮ በኢትዮጵያ መሰማራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ መሃመድ አርካብ አክለውም በኢነርጂ አቅም ግንባታ ዘርፍ ኢትዮጵያውያን የኢነርጂ ባለሙያዎች በአልጀሪያ አቅማቸውን የሚገነቡበት እድል እንደሚመቻች ገልጸዋል፡፡ በቀጣይ ከውሃና ኢርጂ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል፣ ከኢትዮፕያ ኤሌክሪክ አገልግሎት እና ከውጭ ጉዳ ሚኒስቴር በተውጣጣ ቡድን የመግባቢያ ሰነድ በማዘጋጀት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ለነማጠናከር እደሚሰራ ተጠቅሷል፡፡

Share this Post