የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር ፕሮግራም አካሄደ፡፡
መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ.) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበላይ አመራሮች በተገኙበት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የእስልምና እምነት ተከታይ ሰራተኞች ጋር የአፍጥር ስነ-ስርዓት ተካሂዷል።
የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ የተካሄደው አፍጥር በተቋሙ ሰራተኞች መሀል መተሳሰብን የሚያፀና በመሆኑና ሀገራችንም የብዝሀ ማንነቶች መናሃሪያ በመሆኗ ትስስራችን አብሮነታችን፣ ወንድማማችነታችንና እህትማማችነታችንን የሚያጸኑ ድርጊቶች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው፤ አብሮነትን ማጽናት አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል።