በሚቀጥሉት ስድስት ወራት የህዳሴ ግድብ ሪቫን እንቆርጣለን ሲሉ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ገለጹ።
መጋቢት 11/2017ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት የህዳሴ ግድብ ሪቫን እንቆርጣለን ብለዋል።
ህዳሴ ግድብን ብዙ ዋጋ ከፍለንበታል ያሉት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአንድ ብር እርዳታም ሆነ ብድር ከውጭ ያልተገኘበት ፣ብዙ ፈተና ያየንበት ነው ብለዋል።
ህዳሴ ግድብ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ችግር የሚያመጣ አይደለም ፤ የእኛ አላማ ኢነርጂን ማምረት ነው ብለዋል ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
የግብጽ ስጋት ድርቅ እንደሆነ የጠቀሱት ክቡር ጠ/ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ደርቆ ግብጽ ቢዘንብ ዋጋ እንደሌለውና ይልቁንም የአባይ ወንዝ ከኢትዮጵያ ስለሚሄድ ድርቅ እንዳይኖር መከላከል ያለብን ኢትዮጵያ በመሆኑ ለዚህ ደግሞ የግሪን ሌጋሲ ስራችን ማሳያ ነው ብለዋል።
ከግብጽ ወንድሞቻችን ጋር በትብብር አብረን መስራት እና መደጋገፍ እንዳለብን እናምናለን ለውይይትና ለትብብርም በራችን ክፍት ነው ብለዋል።
ህዳሴ ለመላው አፍሪካ መቻልን ያሳየንበት፣ስህተትን ያረምንበት፣ 74 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ የያዝንበት ፣ ከፍተኛ ኢነርጂ የምናመርትበት ፣ አፍሪካውያን ብድር ቢከለከሉና ዲፕሎማቲክ ጫና ቢደረግባቸው የራሳቸውን ሀብት በዜጎቻቸው ማልማትና መቀየር እንደሚችሉ በተግባር የሚያስተምር ኩራታችን ሲሉም ተደምጠዋል።