ኢትዮጵያ ለጋምቢያ በታለቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ልምድ አካፈለች፡፡

ኢትዮጵያ ለጋምቢያ በታለቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ልምድ አካፈለች፡፡ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) በጋምቢያ የማእከላዊ ባንክ ተቀዳሚ ምክትል ገዥ ዶ/ር አብዱላዮ ሲረህ ጃሎ የተመራ ቡድን በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በመገኘት ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ጋር ተወያይቷል፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተሞክሮ ላይ ትኩረት አድርጎ በተካሄደው ውይይት ክቡር ሚነስትሩ ኢትዮጵያ ሀይል ከውሃ የማመንጨት የዳበረ ተሞክሮ እንዳላት አንስተው፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአፍሪካ በትልቅነቱም ሆነ፤ በፋይናንስ ምንጭና ከህዝባዊ ተሳትፎ አንጻር በርካታ ተሞክሮዎች የተገኘበት ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ የህዳሴ ግድብ በመንግስት ቁርጠኝነትና በህዝቦች የነቃ ተሳትፎ በራስ የፋይናንስ አቅም የተገነባና የህዝቦችን አንድነት ያጠናከረ ታላቅ ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንበታ እንዳይሳካ የተደረጉ ጥረቶችን በሙሉ በጥበብ በማለፍ ግድቡ ሀይል ማመንጨት ጀምሯል ብለዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ የድርድር ሂደቶች ጋር ተያይዞ ባደረጉት ገለጻ የአፍሪካን ጉዳዮች በአፍሪካውያን በሚል መርህ የድርድር ሂደቶች የተመሩበት አግባብ ትልቅ ማስተማሪያ ሆኗል በማለት ገልጸዋል፡፡ የጋምቢያ ሉኡካን ቡድን የማእከላዊ ባንክ ተቀዳሚ ምክትል ገዥ ዶ/ር አብዱላዮ ሲረህ ጃሎ ጨምሮ የጋምቢያ የኢኮኖሚና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ሴክሬታሪ የተካተቱበት ነው፡፡

Share this Post