በግድብ ደህንነት ጋይድላይንና አተገባበር ዙሪያ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
መጋቢት 10/2017 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር በግድብ ደህንነት ጋይድላይንና አተገባበር ዙሪያ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደበበ ደፈርሶ ስልጠናውን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ የግድብ ባለቤት ሆነው ግድብ አስተዳደር ላይ የሚሰሩ፣ ግድብ ኦፕሬት የሚያደርጉና የግድብ ደህነንትን ለሚጠብቁ ሶስቱ አካላት በተዘጋጀው የግድብ ደህንነት ጋይድላይንና አተገባበር ዙሪያ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስተባባሪነት የሚሰጥ ስልጠና መሆኑን ገልፀው፤ በግድብ ደህንነት ዙሪያ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ግድብን መንከባከብ፣ መጠበቅና መጠገን እንዲሁም እንዴት መቆጣጠር ይቻላል የሚለው ላይ ግንዛቤ የሚያጨብጥ ስልጠና ነው ብለዋል።
በሚኒስቴር መ/ቱ ሀገሪቱ ላይ ባሉ ግድቦች ላይ ምን አይነት የቁጥጥርና የክትትል ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚችል የሚያስረዳ ጋይድላይን የተዘጋጀ መሆኑን የገለፁት አቶ ደበበ ግድቦች ለሀይል፣ ለመስኖ፣ ለመጠጥ ውሃ አገልግሎት ሲውሉ ኦፕሬት የሚያደርጉ ባለሙያዎችና የከተማ ውሃ አገልግሎቶች በግድቦች ዙሪያ እንዴት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ስልጠና በመስጠት የግድብ ደህንነትን የምናረጋግጥበት ነው ብለዋል።
ግድብ መገንባት ብቻ በቂ ባለመሆኑ ጋይድላይኑ እንዴት ይተገበራል የሚለውን ግንዛቤ ለመፍጠር የአለም ባንክ በቀጠረው "Dam Watch" በሚባል ኮንሰልታንት ስልጠናው እንዲሰጥ ተደርጓል ብለዋል።
ስልጠናው ለሁለተኛ ጊዜ እየተሰጠ ሲሆን፤ በመጀመሪያው ዙር ከኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ከኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ ሃይል፣ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ለተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሰጥቷል።
ለአራት ቀናት በሚቆየው ሁለተኛ ዙር ስልጠና ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያዎች እና የግድብ ደህንነት ተካተዋል። አማካሪዎች ለተከታታይ አራት ቀናት ፡፡