የዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዲጂታል ኤግዝቢሽን ማእከልን ጎበኙ፡፡
መጋቢት 8/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በቦሌ ክፍለ ከተማ የዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዲጂታል ኤግዝቢሽን ማእከልን ጎበኙ፡፡
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ማሙሻ ሀይሉ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተግባርና ሃላፊነት ዙሪያ ገለጻ ለተማሪዎቹ ያደረጉ ሲሆን፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተለይ ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ እንደ አዲስ ሲደራጅ በሶስት መሰረታዊ ዘርፎች፤ ማለትም የውሃ ሀብት አስተዳደር፣ የመጠጥ ውሃ ሳኒቴሽን እንዲሁም የኢነርጂ ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ መደራጀተቱና በጉብኝታቸውም ላይ የነዚህን አተገባበር በዲጂታል ኤግዝቢሽኑ በዝርዝር እንደሚረዱና ስለ ኢትዮጵያ የውሃ እና ኢነርጂ ሀብት እውቀት እንደሚጨብጡ ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎቹን በዲጂታል ኤግዝቢሽኑ በመገኘት ያስጎበኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ጌጡ ስለሀገራችን ውሀ ሀብት መረጃ፣ ስለህዳሴ ግድብ እንዲሁም የኢነርጂ ልማት ላይ ግንዛቤ አስጨብጠዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ያነጋገርናቸው መምህር አቶ አስማረ መኮንን በበኩላቸው ጉብኝቱ በተማሪዎቻችን ላይ ስለ ውሃ ሀበውትና ኢነርጂ ሀብት፤ አባይን ጨምሮ እውቀት እንዲያገኙ ያቻለ ነው ብለዋል፡፡
መምህር አስማረ በማያያዝ እንደ መምህርነቴ ውሃና ኢነርጂ በውሃ ሀብት ዙሪያ ፈር ቀዳጅ ስራ እየሰራ ቢሆንም፤ በቀጣይ ሀገራችን ስላላትና ከጎረቤት ሀገሮች ጋር ስለሚያገናኙን ወንዞች መጪው ትውልድ ላይ በሰፊው በመስራት የድርሻውን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ተማሪ ሀሴት ሰለሞን በጉብኝቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከስሙ ባሻገር ምን እየሰራ እንደሆን ማወቅ ችያለሁ፤ በተለይ ሀገራችን በሚያስፈልጋት መሰረታዊ ነገሮች ላይ ምን እንደተሰራና የመጣውን ለውጥ እንዲሁም ሀገራችን ያላትን የውሃ ሀብት ባጠቃላይ በከርሰ ምድርና ገጸምድርና በገጸምድር ውሃ ሀብት ላይ በሚገባ ግንዛቤ ተፈጥሮልናል ብላለች፡፡
ተማሪ ሀሴት በቀጣይ ስራው የኛ በመሆኑ በውሃ ዙሪያ እንድናውቅና ግንዛቤ እንዲኖረን የመማር እድሉ ቢኖር ጥሩ ነው በማለት ሀሳቧን ገልጻለች፡፡
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሀይድሮሎጅ ዳታቤዝ ባ