መጪው ትውልድ በውሀ ሀብት ላይ ግንዛቤ እንዲኖረው መሰራት እንዳለበት ተገለጸ።

መጪው ትውልድ በውሀ ሀብት ላይ ግንዛቤ እንዲኖረው መሰራት እንዳለበት ተገለጸ። በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ድንበርና ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ስራ አስፈጻሚ ባዘጋጀው የተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብር ላይ መጪው ትውልድ በውሀ ሀብት ላይ ግንዛቤ እንዲኖረው መሰራት እንዳለበት ተገለጸ። ጥር 29/2017 ዓም (ው.ኢ.ሚ) በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የክቡር ሚኒስትር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ማሙሻ ሀይሉ ሀገራችን ያላትን የውሀ ሀብት በተመለከተ ለተማሪዎች እንዲያውቁት ማድረግ በዘርፉ ለመሠማራትና የወደፊት ህልም እንዲኖራቸው ያደርጋል ብለዋል። አቶ ማሙሻ ሀይሉ በማያያዝ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተሠጠው ተግባርና ሀላፊነት ዙሪያ በተለይ በድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ላይ ለተማሪዎች ገለጻ በማድረግ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በተለይ ተማሪዎች ሀገራችን ያላትን የውሀ ሀብት በአግባቡና በመጠቀም ለማልማት እና ለመጠበቅ የሚያስችል እውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ በመግለጽ መርሀ ግሩን አስጀምረዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተቀናጀ ውሃ ሀብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ደበበ ደፈርሶ በተቀናጀ ውሀ ሀብት አስተዳደር ጽንሰ-ሐሳብ፣ መርህ፣ ልምምድ ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል፡፡ በተመሳሳይ ድንበርና ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ በልዩ በበኩላቸው በናይል ተፋሰስ ማህራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ፣ የትብብር መርህ፣ የልማት ቀጠናዊ ትስስር እና ዘላቂነት መርህ፣ ፍትሀዊና ምክኒያታዊ አጠቃቀም በተመለከተ ገለጻ በማድረግ ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም ህብረተሰብ በተለይ ተማሪዎች ስለሀገራቸው የውሀ ሀብት በመረዳት ያገባኛል ማለት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ በግንዛቤ ባስጨበጫ መርሀ ግብሩ ላይ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ባሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ዲጂታል ኤግዚቢሽን ማእከልንም ጎብኝተዋል።

Share this Post