የሚሌ ከተማ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
ጥር 14/2017 (ው.ኢ.ሚ) በአፋር ብሔራዊ ክልል ዞን አንድ ሚሌ ከተማ የተገነባው የንጹህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት የአፋር ብሔራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አወል አርባ አካባቢው ሞቃታማ በመሆኑ ከፍተኛ ውሃ የመጠቀም ፍላጎት እንዳለ አንስተው፤ የሚቀርበውን ውሃ በቁጠባ መጠቀም እንደሚገባ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በበኩላቸው ክልሉ የቱሪስት መዳረሻ ከመሆኑ አንጻር መሰል የውሃ አቅርቦት ስራዎች ለቱሪስት ፍሰት አወንታዊ ሚና እንደሚኖራቸው ጠቁመዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ የከተማው የውሃ አቅርቦት አገልግሎትም በተደራጀ አግባብ መመራት እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡
የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ ክቡር አቶ አህመድ ሻሚ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ለቀጣይ 20 ዓመታት ከ60 ሽህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል፡፡
የሚሌ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከ303 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል፡፡