የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የመጠጥ ውሃና የኢነርጅ ፕሮጀክቶችን ለማየት ድሬዳዋ ገቡ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የመጠጥ ውሃና የኢነርጅ ፕሮጀክቶችን ለማየት ድሬዳዋ ገቡ።

ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም.(ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራ ቡድን በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር፣ በሀራሪ ብሔራዊ ክልል እና በሶማሌ ብሄራዊ ክልል እተተገበሩ የሚገኙ የመጠጥ ውሃና የኢነርጂ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ለመጎብኘትና የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ለማስመረቅ ድሬዳዋ ገቡ።

የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ በድሬደዋ ኤርፖርት በመገኘት አቀባባል አድርገዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ በቆይታቸው የግድቤን በደጀ ፕሮጀክቶችንና የኢነርጅ ፕሮጀክቶቾን የሚጎበኙና የሚያስመርቁ ይሆናል።

በመስክ ጉብኝቱ የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊን ጨምሮ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች ተሳታፊ ናቸው።

በሌላ በኩል ክቡር ሚኒስትሩ የእሳት አደጋ የደረሰበትን የድሬዳዋ ከተማ የአሸዋ ገበያ መዓከልን ጎብኝተዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከጎናቸው በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

Share this Post