በቦረና ዞን ጉቺ ወረዳ ኤርደር ቀበሌ መካከለኛ የመጠጥ ውሀ ፕሮጀክት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተጣለ።

በቦረና ዞን ጉቺ ወረዳ ኤርደር ቀበሌ መካከለኛ የመጠጥ ውሀ ፕሮጀክት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተጣለ።

ግንቦት /2016ዓም (ው.ኢ.ሚ) በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር በመጠጥ ውሀና ሳንቴሽን ዘርፍ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሀ ፕሮጀክት አካል የሆነው በጉቺ ወረዳ ኤርደር ቀበሌ መካከለኛ የመጠጥ ውሀ ፕሮጀክት ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተጣለ።

የመሠረት ድንጋዩን ያስቀመጡት የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ እና የመጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ በጋራ ሲሆን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሀ ፕሮጀክት ተግባራዊ ከሚያደርጋቸው አንዱ ሲሆን፤ በአንድ አመት ተጠናቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል።

የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሀ ፕሮጀክት አካል የሆነው የኤርዳር ቀበሌ ሳይት እና መቲ ሳይትን ጨምሮ ከ83 ሚሊየን ብር በላይ በማውጣት የሚገነባ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ በ10ወር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ እና የመቲ ሳይትን ጨምሮ ወደ 5,000 የህብረተሰብ ክፍሎችን ለ15 ዓመት የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንደሚያደርጎ ተገልጿል።

የቦረና ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ በሪሶ ገኖ በበኩላቸው የውሃ አቅርቦት የዞኑ ትልቁ ችግር መሆኑን አንስተው፤ አሁን ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየሰራ ያለው ስራ የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።

ፕሮጀክቶቹ በአጭር ጊዜ ተጠናቀው የህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ ጥያቄ ይመልሳሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።

Share this Post