የኢጋድ አባል ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች የቶጎ ውጫሌ የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ጎበኙ።
የኢጋድ አባል ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች የቶጎ ውጫሌ የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ጎበኙ።
ሚያዝያ 30/2016 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ.)በሱማሌ ክልል ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ ሙስጠፋ መሀመድ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ኢ/ር ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራ የኢጋድ አባል ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች ቡድን የቶጎ ውጫሌ የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ጎበኝቷል።
የቶጎ ውጫሌ የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት የግንባታው ሥራ በሶማሌ ብሔራዊ ክልል የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን የሥራ ተቋራጭነትና እና በክልሉ የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ቁጥጥር ኢንተርፕራይዞ አማካሪነት እየተገነባ ይገኛል።
ፕሮጀክቱ እኤአ ጥቅምት /2022 ዓ/ም የ5 ጉድጓዶች ቁፋሮ እና ከ51 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የመስመር ዝርጋታ በ490 ሚሊዮን ብር ለመገንባት ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር ውል የተገባ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ አፈጻጸሙ 55% ደርሷል።
ፕሮጀክቱ ተገንብት ሲጠናቀቅ 56 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ከአስተባባሪዎች ገለፃ መረዳት ተችሏል።