ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሀይል ትስስር በመፍጠር የመሪነት ሚና እየተጫወተች መሆኑ ተጠቆመ፡፡

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሀይል ትስስር በመፍጠር የመሪነት ሚና እየተጫወተች መሆኑ ተጠቆመ፡፡

ሚያዝያ 08/2016 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) በአቡዳቢ እ.አ.አ ከአፕሪል 16 እስከ 18 /2024 እየተካሄደ በሚገኘው ወርልድ ፊውቸር ኢነርጂ ሰሚት (world Future Energy Summit) የጎንሽ መድረክ ላይ በመገኘት ገለጻ ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሀይል ትስስር በመፍጠር የመሪነት ሚና እየተጫወተች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የፓንአፍሪካዊ ትብብር ሚና የታዳሽ ሀይል ልማት ከማሳለጥና የኢነርጂ ዋስትና ከማረጋገጥ አንጻር አላማውን አድርጎ በተካሄደው መድረክ ላይ ክቡር ሚኒስትሩ ቀጠናዊ የሀይል ትስስር መሰረት የመጣልና የማጠናከር ጉዳዮች ኢትዮጵያ በቀጠናው ለትብብርና ቅንጅት የሰጠችውን ትኩረት የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸው፤ እንደተጨማሪ ማሳያም ሱዳናውያን የገጠማቸው ውስጣዊ ችግር ክፍያ እንዲፈጽሙ ባያስችላቸውም የሀይል አቅርቦት መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም ኢትዮጵያ ከልማት አጋሮች ጋር በመሆን የምስራቅ አፍሪካ ፓወር ፑል ለማጠናከርና ለማስቀጠል አይነተኛ ሚና እየተጫወተች ነው ያሉ ሲሆን፤ የሀይል መስመሮች መንገዶችና የቴሌኮም ኔትወርኮችን የመሳሰሉ መሰረተልማቶች ወደ ጎረቤት ሀገራት ተዘርግተው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ብሔራዊ እቅድ ቀጠናዊ ቅንጅታዊ እስትራቱጂ መካተቱንና በአህጉር ደረጃ ማሳደግ ታሳቢ መደረጉን አንስተው፤ እንደሃገር ያለን የሀይድሮፓወር እምቅ አቅምና የማልማት ልምድ፤ እንዲሁም በሃድሮ ፓወር ልማት የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው ተቋም መገንባት መቻሉ፤ የምስራቅ አፍሪካ የአረንጓዴ ኢነርጂ ማእከል ለመሆን እንድንሰራ አስችሎናል ብለዋል፡፡

የመንግስትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት በመተግበር የግሉን ዘረፍ በሃይል ልማት ዘርፍ ለማሳተፍ ያለውን ቁርጠኝነት አንዱ ማሳያ መሆኑን ያነሱት ክቡር ሚኒስትሩ፤ የኢትዮጵያ አህጉራዊ የሀይል ሲስተም ማስተርፕላን መሰረት በማድረግ ለሶስት ጎረቤት ሀገራት የሀይል ትስስር መፈጠሩንና ሌሎችን ሀገራትን በማካተት ወደ አህጉራዊ ትስስር ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የሀይል መሠረተልማት ግንባታና ዝርጋታ ከፍተኛ መዋእለንዋይ የሚጠይቅ በመሆኑ የልማት አጋሮች ቁርጠኝነት እጅግ አሰእፈላጊ መሆኑን አስታውሰው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በሀይል ልማት ኢንቨስትመንት መሰማራት በቀጠናው የስራ እድል ፈጠራ እና የሰላምና የጸጥታ ጉዳች ላይ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው ብለዋል።

Share this Post