የብሄራዊ የመጠጥ ውሃ፣ የሳኒቴሽን እና የኃይጅን የፕሮግራም ዝግጅት የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

የብሄራዊ የመጠጥ ውሃ፣ የሳኒቴሽን እና የኃይጅን የፕሮግራም ዝግጅት የምክክር መድረክ ተካሄደ ፡፡

ሚያዝያ 04/2016 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) ብሄራዊ የአንድ ቋት (One WaSH) የመጠጥ ውሃ፣ የሳኒቴሽን እና የኃይጅን የፕሮግራም ዝግጅት የምክክር መድረክ ተካሄደ ፡፡

የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ በለፉት አመታት መንግስት ለዜጎች ፍትሃዊ እና ዘላቂ በሆነ መልኩ ንፁህ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በፖሊሲና በስትራተጂ የተደገፈ ተጨባጭ ሥራዎችን ማከናወኑን ገልፀዋል።

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘውም የፕሮጀክት አፈፃፀም የሚያሻሽሉ ብሄራዊ የአንድ ቋት (One WaSH) አሰራር ከመቅረፅ ጀምሮ የዋሽ ሴክተር ፈፃሚዎችን በማቀናጀት እና በማስተባበር መንግስት ከፍተኛ ሚና መወጣቱን አስረድተዋል።

በሌላ በኩል መንግስት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በተከታታይ በንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ቢቻልም አሁንም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የህብረተሰብ ክፍል ንፁህ የመጠጥ ውሃ፣ የሳኒቴሽን እና የኃይጅን አገልግሎት ተደራሽ የማድረግ ውስንነት መኖሩን ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አንስተው፤ የአለም ባንክ እና የልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በቀጣይ 10 ዓመታት የሚተገበር ውጤት ተኮር የፕሮግራሙ አዲስ አፈጻጸም ሞዳሊቲ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ዶ/ር ከበደ ገርባ በበኩላቸው ፕሮግራሙን ከአለም ባንክ በተገኘው 500 ሚሊዮን ዶላር እ.አ.አ. ከ2025 እስከ 2035 ዓ/ም ለቀጣይ 10 ዓመታት 118 ወረዳዎች ላይ ተግበራዊ ለማድረግ መያዙን ለተሳታፊዎች ገለፃ አድርገዋል።

የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ አያይዘውም ባለፋት 15 ዓመታት ግብዓት ተኮር (Input based) ላይ የተመሠረተ የተግባራት ክዋኔዎች ላይ ያተኮረ እንደነበር ገልፀው፤ አዲሱ የፋይናንስ ሞዳሊቲ ውጤት ተኮር (Results based) የክፍያ ስርዓት እንደሚሆን አስረድተዋል። የአዲሱ ብሄራዊ የአንድ ቋት (OneWaSH) ፕሮግራም ከነባሩ ያለውን ልዩነትና ጠቀሜታው ሲያስረዱ ነባሩ ፕሮግራም የውሃና ሳኒቴሽን ተቋማት ግንባታ ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ አዲሱ ፕሮግራም በተገነቡት ተቋማት አገልግሎት ያገኙት የህብረተሰብ ክፍሎችን እና ተቋማቱ በዘለቄታዊነት አገልግሎት መስጠት መቻላቸውን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

Share this Post