አንድን ተፋሰስ የእቅድ ማእከል በማድረግና ተዋናይ የሆኑ አካላትን በማሳተፍ የተቀናጀ ውሀ ሀብት አስተዳደርን ወደ መሬት ማውረድ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

አንድን ተፋሰስ የእቅድ ማእከል በማድረግና ተዋናይ የሆኑ አካላትን በማሳተፍ የተቀናጀ ውሀ ሀብት አስተዳደርን ወደ መሬት ማውረድ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ሚያዚያ 04/2016ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ በብሄራዊ የተቀናጀ ውሀ ሀብት አስተዳደር የአንድ ተፋሰስ አንድ እቅድ አተገባበር ዙሪያ ከክልል ባለድርሻ ቢሮዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ፡፡

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሀ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ አንድን ተፋሰስ የእቅድ ማእከል በማድረግና ተዋናይ የሆኑ አካላትን በማሳተፍ የተቀናጀ ውሀ ሀብት አስተዳደርን ወደ መሬት ማውረድ እንደሚገባ ገልጸው፤ ባለድርሻ አካላቱ ከመጀመሪያ ጀምሮ የሚሳተፉበት እና ከእቅዱ እየተመነዘረ እያንዳንዱ ሴክተር ስራውን የሚያይበት ፕሮግራም ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ዲኤታው በማከል ዋና ባለድርሻ አካላት ከፕላንና ልማት ከግብርና፣ ከመስኖ፣ ከአካባቢ ጥበቃ እና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ወክለው የሚሰሩ በሁሉም ተፋሰስ ያሉ የክልል ውሃ ቢሮ አካላት ያሉበት የወርኪግ ግሩፕ በማቋቋም ስራዎችን ከፌደራል እስከ ወረዳ በማውረድ ስለ ውሃ ሀብት አስተዳደር አጠቃቀም እንዲረዱ በማድረግ ሁሉም የራሳቸውን ድርሻ በመውሰድ ውሀን መሰረት ያደረገ የቴክኒክ ፎረም በመመስረት በባለቤትነት እንዲሰሩ ማስቻል ከናንተ ይጠበቃል በማለት ውይይቱን አስጀምረዋል፡፡

መርሀ ግብርሩ ላይ በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሀ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶክተር አብርሃ አዱኛ የውሃ ሀብት አስተዳደር ታሪካዊ አመጣጥ በኢትዮጵያ በሚል የተዘጋጀውን ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን፤ በዚህም የተቀናጀ ውሀ ሀብት የነበረበትን እና አሁን ያለበት ደረጃ በደረጃ ገለጻ በማድረግ በተለይ በኢትዮጵያ ውሀን መጠቀም፣ ማልማት፣ መጠበቅና መቆጣጠር እንዲሁም ወደ ክፍያ ስርት ማስገባት በሚቻልበት እና በሌሎች ውሀ ነክ ተግባሮች ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ በብሔራዊ የተቀናጀ የውሀ ሀብት አስተዳደር፣ ተግዳሮቶች እና መልካም አጋጣሚዎች፣ የተፋሰስ እቅድ ፕሮግራም የበጀት እና የቁልፍ አፈጻጸም ሪፖርት፤ እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ሰነዶች ቀርበው ውይይት የተደረገ ሲሆን ፕሮግራሙ በነገው እለትም ቀጥሎ ይውላል፡፡

Share this Post