የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ፡፡

መጋቢት /2016 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ‹‹ማርች 8›› የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች ”ሴቶችን እናብቃ፣ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል አክብረዋል፡፡

በእለቱ ንግግር ያደረጉት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የክቡር ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሻ ኃይሉ ሴቶች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አበረታች ተግባራትን እያከናወነ ነው ብለዋል፡፡ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግና ተጠቃሚነታቸውንም ለማረጋገጥ ሥራዎች ታቅደው እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡

በተያያዘ ዜና የሴቶች ማህበራዊ ጉዳይና አካቶ ትግበራ ስራ አስፈጻሚ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ ደረጃውን የጠበቀ የህጻናት ማቆያ ማዕከል በማደራጀት አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ ነው። በዚህም የተደራጀና ምቹ የህጻናት ማቆያ በማዘጋጀት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ማዕከሉ እድሜያቸው ከ6 ወር እስከ 3 ዓመት ያሉ እና የተቋሙ ባልደረባ የሆኑ ወላጆች ህጻናትን ተቀብሎ ሳይንገላቱ ልጆቻቸውን ከጎናቸው አድርገው ስራቸውን የሚያከናውኑበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላቸዋል።

በእለቱ በማቆያ ማዕከሉ የልጃቸውን ልደት ሲያከብሩ ያገኘናቸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባልደረባ ወ/ሮ ትእግስት ማሞ በማዕከሉ አገልግሎት አሰጣጥ ከመርካታቸው በላይ ህጻናቱ ከሞግዚቶቹ ጋር ባላቸው እናታዊ መስተጋብር በእጅጉ መደሰታቸውን ገልጸው ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ለወላጆች በተለይም ለሴቶች ለሚያደርገው ድጋፍና እንክብካቤ ሊመሠገን ይገባዋል ብለዋል።

በመጨረሻም መጋቢት 13 የ3ተኛ ዓመት ልደቷን በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የህጻናት ማቆያ ያከበረችውን ህጻን መክሊት መልካም ልደት ለማለት እንወዳለን።

Share this Post