የክትትል እና ድጋፍ ቡድኑ በባካ ዳውላ አሪ ወረዳ የመስክ ምልከታ አደረገ።

የክትትል እና ድጋፍ ቡድኑ በባካ ዳውላ አሪ ወረዳ የመስክ ምልከታ አደረገ።

የፌዴራል ሱፐርቭዥን ቡድን በወረዳው ሦስት ቀበሌዎችን በሚጎበኙበት ወቅት የኢፌዴሪ ውሃና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የጉብኝቱ ዋና አላማ ተሞክሮዎችን ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል በማስፋፋት ተያይዞ ለማደግ እንደሆነ ገልፀዋል።

ጉድለቶችን ነቅሶ በማውጣት እና በማረም የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያለመ ስለመሆኑም አንስተዋል።

በተጨማሪም ዞኖችና ወረዳዎች ምን አቅም አላቸው ምንስ ይጎድላቸዋል የሚለውን ለማወቅ የሚያስችል ስለመሆኑ ሚንስቴሩ አስረድተዋል፡፡

በአሪ ዞንና በወረዳ ከተማ መስተዳደሮች የጉብኝት የትኩረት መስክ ከሆኑት መካከል የእርቀ ሠላም ሥራዎች ያሉበት ደረጃ፤የበጎ አድራጎት ሥራዎች ህብረተሰብን በማሰባሰብ የመሥራት ባህላችን ከማሳደግ አንፃር ያለውን እንቅስቃሴ፣የአረንጓዴ አሻራ ሥራዎች ምልከታ ይገኙበታል።

Share this Post