በዋርዴር ወረዳ ኩርቱሌ ቀበሌ የሶላር ኢነርጂ ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት በቅርቡ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገለጸ።

በዋርዴር ወረዳ ኩርቱሌ ቀበሌ የሶላር ኢነርጂ ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት በቅርቡ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገለጸ።

የካቲት 29/2016ዓ.ም(ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጅ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ የተመራ ቡድን በሶማሌ ክልል ዋርዴር ወረዳ ኩርቱላ ቀበሌ እየተገነባ ያለውን የአማራጭ ኢነርጂ ቴክኖሎጅ የሶላር ኢነርጂ ሚኒ ግሪድ ፕሮጀክት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ ተቋሙ የኢነርጂ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ በተለይ ከግሪድ ውጭ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሀይል ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ አማራጭ ኢነርጂ ላይ እየተሰራ መሆኑንና እየተገነቡ የሚገኙ የሶላር ቴክኖሎጂ፣ የባዮ ጋዝ እንዲሁም የንፋስ ሀይል ማሳያ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው ከፍተኛ የሆነ የጸሀይ ሀይል ሀብት በሚገኝበት በሶማሌ ክልል በዋርዴር ወረዳ ኩርቱሌ ቀበሌ እየተገነባ ያለው ፕሮጀክት በቅርቡ ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚሰጥ ጠቅሰው በዚህ ፕሮጀክት የአካባቢውን ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን ይፈታል ብለዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው በማያያዝ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር 140 ኪሎዋት ሀይል የሚያመነጭ ሲሆን፤ ዘጠኝ መቶ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

አቶ አብዲ ኤሪክ የተባሉ አካባቢው ነዋሪ ከፍተኛ የሆነ የመብራት እጥረት እንዳለባቸው ገልጸው ፕሮጀክቱ ቶሎ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር፤ በሙቀት ምክንያት የሚፈጠርብንን ማህበራዊ ጫና ይቀንስልናል ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ፕሮጀክቱን በባለቤትነት በመውሰድ አስፈላጊውን ጥበቃ ጭምር የምናደርግ መሆኑን ለማረጋገጥ እፈልጋለሁ ብለዋል።

ፕሮጀክቱ ከአውሮፓ ህብረት በተገኘ 63 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ በ GIZ አስተባባሪነት ከፌደራልና ከክልሉ መንግስት ጋር በጥምረት እየተሰራ መሆኑን ማወቅ ችለናል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የውሀና ኢነርጂ የኢነርጂ ዘርፍ አመራሮና ባለሙያዎች፣ የክልሉ የኢነርጂ ሀላፊ ፣ የሚደዲያ አካላት ፣ እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተሳትፈውበታል፡፡

በመጨረሻም የመስክ ጉብኝቱ በተለያዩ ክልሎች እንደሚቀጥል ከአስተባባሪዎች ማወቅ ተችሏል።

Share this Post