የከተማ ውሃ አቅርቦት ጥናትና ዲዛይን መመዘኛና መለኪያ ጋይድላይን ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።

የከተማ ውሃ አቅርቦት ጥናትና ዲዛይን መመዘኛና መለኪያ ጋይድላይን ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።

የካቲት 28/2016 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የከተማ ውሃ አቅርቦት ጥናትና ዲዛይን መመዘኛና መለኪያ ጋይድላይን ውይይት እየተካሄደ ነው።

የውይይቱን መድረክ በንግግር የከፈቱት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ የከተማ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ጥናትና ዲዛይን ጋይድላይን ችግር ፈቺ እንደሚሆን ገልፀው፤ በመድረኩ የሚሰጠው አስተያየት ዶክመንቱን በማጠናከር የበለጠ እንዲዳብርና የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ይሆናል ብለዋል።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃ አቅርቦት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ታምሩ ገደፋ እንደገለፁት የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ተቋሙ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ በመሆኑና የመጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ጥናት እየተደረገ መሆኑን ገልፀው፤ ቼክሊስቶችን በማዘጋጀትና በዘርፉ የሚሰሩ አካላት ጥናት እንዲያካሄዱ በማድረግ እ.ኤ.አ በ2006 የነበረውን የከተሞች የመጠጥ ውሃ ጥናትና ዲዛይን መመዘኛ ጋይድላይን ለማሻሻልና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስገባት የተዘጋጀ ዶክመንት መሆኑን ገልፀዋል።

የMS Consultant አስተባባሪ ወ/ሮ ሀመረ ወንድሙ በበኩላቸው ዶክመንቱን ለማዘጋጀት የአንድ አመት ውል የተገባ ቢሆንም ለማጠናቀቅ ብዙ ውይይትና ግምገማ የሚፈልግ ስራ በመሆኑ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁን ገልፀዋል።

ወ/ሮ ሀመረ አያይዘውም የተዘጋጀው ዶክመንት በአገር አቀፍ ደረጃ ለክልሎችና በውሃው ሴክተር ለተሰማሩ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመው፤ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ዶክመንቱን በመገምገም ሂደት ለነበረው ተሳትፎ አመስግነዋል።

በመድረኩ የዲዛይን መስፈርቶችና መመሪያዎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፤ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች፣ የግል ድርጅቶች፣ የውሃ አገልግሎት ተቋም ተወካዮች፣ ኮንትራክተሮችና ኮንሰልታንቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

Share this Post