በስምጥ ሸለቆ ሐይቆች በሰገን ወንዝ ላይ ለሚገነባ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የቅድመ ጥናት ረቂቅ ሪፖርት ለውይይት ቀረበ።

በስምጥ ሸለቆ ሐይቆች በሰገን ወንዝ ላይ ለሚገነባ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የቅድመ ጥናት ረቂቅ ሪፖርት ለውይይት ቀረበ።

የካቲት 28/2016 ዓ/ ም በስምጥ ሸለቆች ሐይቆች የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የቅድመ ጥናት ረቂቅ ሪፖርት ለውይይት ቀረበ።

አውደጥናቱን በንግግር የከፈቱት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ሀብት ጥናት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሌብ ታደሰ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና በፌዴራል ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የውሃና ኢነርጂ ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ዘርፍ የፕሮጀክቱ ዲዛይን ጥናት በመካሄድ ላይ መሆኑን ገልፀው፤ በመጀመሪያ የጥናት ረቂቅ ላይ ከባለድርሻ ጋር ውይይት በማድረግ ጥናቱን የሚያዳብሩ ግብዓት ለማሰባሰብ ያለመ ነው ብለዋል።

መሪ ስራ አስፈፃሚው አያይዘውም የፕሮጀክቱ ዋና አላማ የውሃ ኃይል ማመንጫ መገንባት ቢሆንም፤ የውሃ ሀብቱ ለመስኖና ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት መዋል የሚያስችል አቅም እንዳለው አስረድተዋል።

በውሃና ኢነርጂ ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ዘርፍ የፕሮጀክቱ አስተባባሪው አቶ ኤልያስ አስታጥቄ በበኩላቸው፤ የአውደጥናቱ አላማ በስምጥ በሸለቆ ሐይቆች ውስጥ በሰገን ወንዝ ላይ የሚገነባው የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የቅድመ ዲዛይን ጥናት ረቂቅ ለባለድርሻ አካላት ገለፃ ማድረግ እና የጥናት ግብዓት ለማሰባሰብ ያለመ ነው ብለዋል።

አስተባባሪው አክለውም የሃይድሮሎጂ፣ የአከባቢ ተፅዕኖ እና ሌሎች የቅድመ ጥናት ረቂቅ ጥናቶች ቀርበው ምክክር የሚካሄድባቸው መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይ የጂኦቴክኒክ ምርመራን ጨምሮ ቀሪዎቹን ስራዎች አጠናቀን እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ/ም ድረስ ለማቅረብ እየሰራን ነው ብለዋል።

አስተባባሪው ጥናቱ የሚካሄድበት አካባቢ የመንገድ መሠረተ ልማት ውስንነት በመኖሩ ጥናቱን በማፋጠን ሂደት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል።

Share this Post