በሞጆ ከተማ አስተደደር በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ድጋፍ ለአቅመ ደካሞች የተገነባ መኖሪያ ቤት ለተጠቃሚዎች ቁልፍ ርክክብ ተደርጓል።

በሞጆ ከተማ አስተደደር በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ድጋፍ ለአቅመ ደካሞች የተገነባ መኖሪያ ቤት ለተጠቃሚዎች ቁልፍ ርክክብ ተደርጓል።

የካቲት 20 /2016 ዓ/ም(ው.ኢ.ሚ ) በሞጆ ከተማ አስተደደር በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ድጋፍ ለአቅመደካሞች የተገነባ መኖሪያ ቤት ፕሮጀክት ተመርቆ ለተጠቃሚዎች ቁልፍ ርክክብ ተደርጓል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ የዛሬ 5 ዓመት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ያስጀመሩት የማዕድ ማጋራት፣ የአረንጓዴ አሻራ እና የአቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት እድሳት ኢኒሸቲቭ መሠረት በማድረግ የቤት እድሳቱ መጀመሩን ገልጸው፤ ባለፈው ክረምት በሞጆ ከተማ አካባቢ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ላይ የቤት እድሳት መርሃግብሩ እንዲጀመር መወሰኑን ገልጸዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ የመኖሪያ ቤት ለተሰራላቸው የቤት ቁሳቁስ እንደሚሟላለቸው ገልፀው፣ በዕለቱም ለ25 አቅመ ደካሞች ሙሉ አልባሳት ድጋፍ ተደርጓል ።

የሞጆ ከተማ ከንቲባ አቶ ጋዝአሊ አሹ በበኩላቸው 6 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ለተደረገው የአቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት እድሳት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትርን ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙን አመስግነው፤ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በጎ አድራጎትን ተከትሎ የተለያዩ አካለት አቅመ ደካሞች ለመርዳት መነሳሳት መፈጠሩን ከንቲባው ገልፀዋል።

ክቡር ከንቲበው ጨምረውም የሞጆ ከተማ የውሃ ችግር እንዲያግዙ ለክቡር ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል።

አበባ ዋጋሪ ሁለት ልጆች እናት ስትሆን አካል ጉዳተኛ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የመኖሪያ ቤቷ ምቹ ባለመሆኑ ለከፍተኛ እንግልት ስትዳረግ እንደነበር ገልጻ፤ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በተደረገላት የመኖሪያ ቤት እድሳት ተጠቃሚ በመሆኗ መደሰቷንና ለተደረገላት ድጋፍ ምስጋና አቅርባለች።

Share this Post