''ሴቶችና አመራርነት'' በሚል ርዕስ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሴቶች ስልጠና እየተሠጠ ነው።

''ሴቶችና አመራርነት'' በሚል ርዕስ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሴቶች ስልጠና እየተሠጠ ነው።

የካቲት 22/2016ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) ለውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴር ሴት አመራርሮችና ባለሙያዎች ''ሴቶችና አመራርነት'' በሚል ርዕስ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በስልጠናው መጀመሪያ ንግግር ያደረጉት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኦልቀባ ባሼ ሴቶችን ወደ አመራር ሰጭነት ለማምጣት እና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እንዲሁም በአመራር ላይ ያሉ ሴቶችን ደግሞ ብቃታቸውን ለማሳደግ ታላሚ ያደረገ ነው ሲሉ የስልጠናውን አስፈላጊነት ገልጸዋል።

ሴቶች አመራር ሲሆኑ በቤተሰባዊነት ስሜት ስለሚቀርቡ ውጤታማ እንደሚሆኑ ጥናቶች እንደሚያመላክቱ የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው ስልጠናው ተወዳዳሪ ፣ ተነሳሽነት እና ሞራላቸው የተገነባ ሴቶችን ወደ አመራርነት በማምጣት ተቋምን ውጤታማ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የጎላ ድርሻ እንዲኖራቸው ለማስቻል የታለመ ስልጠና በመሆኑ ሁሉም በንቃት እንዲሳተፍ አሳስበዋል።

ስልጠናው በዋናነት አመራርነት ምንድነ ነው፤ እንደ ስራ አመራር ልንገነዘባቸው የሚገቡ ነጥቦች፤ ለአመራርነት አስፈላጊ በሆኑ መሰረታዊ ነጥቦች፤ ራስን መምራትና በሌሎች ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ በዶ/ር ተመስገን ዳኜ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በስልጠናው ላይ የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሴት አመራሮችና ባሙያዎች እንዲሁም የተጠሪ ተቋማትና የቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ሰራተኞች ተሳትፈውበታል፡፡

Share this Post