የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ከዋልታ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ከዋልታ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡

የካቲት 18/2016 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ.) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ከዋልታ ሚዲያ ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት አመራሮች ጋር የውሃና ኢነርጂ ጉዳዮችን ሚዲያን ተጥቅሞ ዜጎችን ከማስተማርና ዘርፉን ከማስተዋወቅ አንጻር ውይይት አድርገዋል፡፡

ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ስለውሃ ሀብት እና ስለኢነርጂ ሀብት ለዜጎች ማሳወቅ አስፈላጊነትን አንስተው፤ ሚዲያ ትልቅ ሚና መጫወት እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም በቀጣይ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁነቱ እንዳለ ተናግርው፤ የውሃ፣ የውሃዲፕሎማሲ እና ኮሚኒኬሽን ፎረም ሲቋቋም በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ሚዲያው የሚኖረውን ሚና ታሳቢ በማድረግ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

የዋልታ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መሃመድ ሀሰን ስለውሃ አለመአቀፍ ሚዲያዎች አጀንዳ በሚያደርጉት ልክ በሀገር ደረጃ አጀንዳ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ ደረጃቸውን የጠበቁ ዶክመንታሪዎችንና ሌሎች የህትመት ውጤቶችን በማዘጋጀት በሚፈለገው ልክ አጀንዳ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

Share this Post