የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ፎረም መመስረቻ ደንብ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ፎረም መመስረቻ ደንብ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተግባራዊ በሚያደርጋቸው የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን፣ ኢነርጂ ተደራሽነት፤ እንዲሁም በተቀናጀ የውሀ ሀብት አስተዳደር ላይ በሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ዙሪያ ያሉ ሂደቶችን በተለያዩ የኮሙዩኒኬሽን አግባቦች ለህብረተሰቡ ወጥ በሆነ መልኩ ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል ፎረም ለመመስረት ውይይት ተካሄደ፡፡

የካቲት 15/2016ዓም(ው.ኢ.ሚ) መርሀ ግብሩን በንግግር ያስጀመሩት በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የክቡር ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሻ ሀይሉ የዛሬው አጀንዳ ስራችንን ለማስፋት ከክልሎች ጋር በቅንጅት የበለጠ ለማጠናከር፤ የምንሰራቸው ስራዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ መመሪያውን በዚህ ደረጃ ለማስፈጸም ታስቦ የተዘጋጀ የውይይት መድረክ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ማሙሻ በማከል በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የምንሰራቸው ስራዎች በመንግስትና በህዝብ ሀብት የሚተገበሩ ወሳኝና ለህይወት አስፈለጊ ስለሆኑ ለህብረተሰቡ ግልጽና ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊና ወሳኝ በመሆኑ በተበታተነ ሁኔታ ከምንሰራ በቅንጅት መስራት ውጤታማ ሊያደርገን ስለሚችል ደንብን በጥልቀት እንድትከታተሉ በማለት አሳስበው መድረኩን አስጀምረዋል ፡፡

የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ጌጡ የመመስረቻ ደንቡን ያቀረቡ ሲሆን የፎረም ምስረታው በዋናነት በክልሎች እና በተጠሪ ተቋማት የተቀናጀና የተናበበ ስራ ለመስራት፣ ስራዎች ፓሊሲ መሠረት ያደረጉ እንዲሆኑ፣ በፎረሙ አባላት መካከል መግባባትን ለመፍጠር፣ በዲጂታል ሚዲያ ስራዎችን ለማካተት እና በሁሉም ቋንቋ ተደራሽ በማድረግ በየደረጃው ወጥ የአሰራር ሥርዓት ለመዘረጋት መሆኑን አስታውቀዋል ።

የፎረሙ መመስረቻ ደንቡ ላይ ተሳታፊዎች በጥልቀት በመወያየት ፎረሙን ሊያዳብሩ የሚችሉ ገንቢ ሀሳብ አስተያየት ሰጥተውበታል።

በመድረኩ ላይ የውሀና ኢነርጅ ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልል የውና ኢነርጂ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች የተጠሪ ተቋማት ስራ አስፈጻሚና ባለሙያዎችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካለት ተሳትፈውበታል፡፡

Share this Post