የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ምእራፍ የመስክ ሪፖርት ላይ ውውይት ተደረገ፡፡

የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ምእራፍ የመስክ ሪፖርት ላይ ውውይት ተደረገ፡፡

የካቲት/2016ዓም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ምእራፍ እስካሁን ያለውን አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የብሔራዊ ዋን ዋሽ አስተባባሪ የሆኑት አቶ አብይ ግርማ ሪፖርቱን ከሚመለከታቸው ሴክተሮች የተውጣጡ 6ቡድን በእያንዳንዱ ክልል ላይ በመሄድ ከፌደራል ሴክተር መስሪያ ቤቶች እና አጋር ድርጅቶች ከሆኑት አለም ባንክ፤ የእንግሊዝ መንግስት፤ ዩኒሴፍ፤ ኔዘርላንድ ኤምባሲ እና ከሌሎች ጋር በመሆን የፕሮግራሙ አፈጻጸም መሬት ላይ ምን ይመስላል የሚለውን በመገምመ ያሉትን ጠንካራ ጎኖች እና ድክመቶችን በመገምገም ለየክልሉ የውሃና ሳኒቴሽን ዋሽ ስትሪንግ ኮሚቴ አባላት፤ ለቢሮ ሀላፊዎች በማቅረብ አፈጻጸም ለማሻሻል ታሳቢ ተደርጎ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

አስተባባሪው በማከል ከየክልሉ የመጡ ቡድኖች ያቀረቡትን ግኝት ለመድረኩ በማቅረብ ውይይት ይደረግና ድክመቶችን በማረም ጥንካሬዎችን ይበልጥ አጠናክረን የምንቀጥልበት ይሆናል በማለት ገልጸዋል፡፡

አቶ አብይ በመጨረሻም ፕሮግራሙ ሊጠናቀቅ አንድ አመት የቀረው በመሆኑ ቀጣዩ ፕሮግራም ምን ይመስላል፤ ምን አይነት አፈጻጸሞች ይኖሩታል፤ ምን ምን ያካትታል፤ የሚለው በዚሁ መድረክ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ ከውሀና ኢነርጂ፤ ከፌደራል መንግስት፤ ከጤና፣ ከትምህርት፣ ከፋይናንስ የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም አስተባባሪዎች ተሳትፈውበታል፡፡

Share this Post