''የውሃ ሀብታችን ለብልፅግናችን'' በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው ሀገራዊ ኤግዚብሽን ላይ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና መርሀ ግብር ተካሔደ፡፡

''የውሃ ሀብታችን ለብልፅግናችን'' በሚል መሪ ሀሳብ በተዘጋጀው ሀገራዊ ኤግዚብሽን ላይ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና መርሀ ግብር ተካሔደ፡፡

የካቲት 12/2016 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ጋር በጋራ ባዘጋጁት ሀገራዊ ኤግዚብሽን ላይ በተለያየ አግባብ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች የምስጋና መርሀ ግብር ተካሄደ።

መርሀ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከለውጥ ጀምሮ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወን መቻሉን ገልጸው፤ በአይነቱ ልዩ የሆነና ስኬታማ ስራዎቻችንን ያስተዋወቅንበት በመሆኑ በስራው ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦችን እውቅና በመስጠት አጋርነታችንን ለማሳየት የታሰበ ነው ብለዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም ኤግዚብሽኑ ዘላቂ የውሃ ሀብታችንን እንዴት እንደምናስተዳድር፣ የኢነርጂ ልማትን በማስፋፋት፣ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘረፍ የሚከናወኑ ስራዎቻችንን ለማስተዋወቅ ትልቅ እድል የፈጠረልን ነው ብለዋል።

በመርሀ ግብሩ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም በተለያየ አግባብ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች የእውቅናና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

ለተከታታይ ሰላሳ አምስት ቀናት ለእይታ ክፍት የነበረው ኤግዚቢሽን ከ282 ሺ በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ዜጎች ጎብኝተውታል።

Share this Post