የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በደቡብ ኮሪያ በሚካሄደው የዓለም አቀፍ የአካባቢ፣ ማህበራዊና የአስተዳደር ፎረም ላይ ተሳተፉ ፤

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በደቡብ ኮሪያ በሚካሄደው የዓለም አቀፍ የአካባቢ፣ ማህበራዊና የአስተዳደር ፎረም እየተሳተፉ ይገኛሉ፤ የኢፌዲሪ ውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በደቡብ ኮሪያ, ሲዎል እ.ኤ.አ ከኦገስት 29 እስከ 31/2022 በሚካሄደው የዓለም አቀፍ የአካባቢ፣ ማህበራዊና የአስተዳደር ፎረም (2022 Environment, Social and Governance Forum) ለመሳተፍ ደቡብ ኮሪያ ተገኝተዋል። ክቡር ሚንስትሩ በአብይ ጉባኤው መድረክ ላይ የአየር ንብርት ለውጥ በኢትዮጵያ እያስከተለ የሚገኘውን አደጋ እንዲሁም እየተወሰደ የሚገኘውን የመፍትሄ አቅጣጫ አስመልክቶ ጽሁፍ የሚያቀርቡ ሲሆን በቆይታቸው የፕሮጀክት ትብብር ስምምነቶችን ከኮሪያ የውኃ ኮርፖሬሽንና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር ይፈራረማሉ። ክቡር ሚኒስተርሩ ፎረሙ በይፋ ከከፈቱት ከቀድሞ የተመድ ዋና ጸሐፊ ባን ኪሙን ጋር ተገናኝተው በአካባቢ ጥበቃና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የተነጋገሩ ሲሆን በተመሳሳይ ከተመድ የአየር ንብረት ፕሮግራም ዳይሬክተር ጃሚል አህመድ ጋር በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራምና አካባቢ ጥበቃ ሥራ ተወያይተዋል። ከዚህ በፊት ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ሰኔ 6 ቀን 2014 ዓ/ም የደቡብ ኮሪያን የውኃ ኮርፖሬሽን የአውሮፓና የአፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑትን ዶ/ር ሺን ኪንግሺንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው በሁለትዮሽ የትብብር ዕድሎች ላይ መወያየታቸው ይታወሳል።

Share this Post