የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከደ/ኮሪያ ውኃ ኮፖሬሽን ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ።
የውኃና ኢነርጂ ሚንስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ከኮሪያ ውኃ ኮርፖሬሽን ፕረዚደንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፓርክ ጄይ ጋር የትብብር ስምምነት በደ/ኮሪያ፣ ሲዎል ተፈራርመዋል።
ፕረዚደንቱ በስምምነት ንግግራቸው የኢትዮጵያና ኮሪያ ግንኙነት እንደማንኛውም ሀገር የዲፕሎማሲና የልማት ትብብር ብቻ ሳይሆን በደም የታተመ መሆኑን አንስተው ኮርፖሬሽኑ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር በአጋርነት ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
ክቡር ሚንስትሩ በበኩላቸው ፕረዚደንቱ ያነሱትን የሁለትዮሽ ግንኙነት አረጋግጠው ከድርጅቱ ጋር በውኃና ኢነርጂ ዘርፍ በቅርበት መስራት እንደሚፈልጉ ገልጸውላቸዋል።
የድርጅቱ ፕረዚደንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ በጥቅምት ወር 2015 ዓ/ም ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።