የውሃና ኢነርጂ ሀገራዊ ኤግዚቢሽን ሊጠናቀቅ ሰአታት ቀሩት።

የውሃና ኢነርጂ ሀገራዊ ኤግዚቢሽን ሊጠናቀቅ ሰአታት ቀሩት። መስከረም/2016 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ)የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የስራ እድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ/ቤት አመራሮች፣ ሠራተኞች እና በክፍለ ከተማው በተለያዩ ዘርፎች የተደራጁ በርካታ ማህበራት "የውሃ ሀብታችን ለብልፅግናችን" በሚል መርህ ሲጎበኝ የቆየው የውሃና ኢነርጂ ኤግዚብሽን ሳይንስ በመገኘት ጎበኙ። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ጋር በመተባበር በሳይንስ ሙዚየም ያዘጋጁት ሀገራዊ የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሽን ለ35 ቀናት በርካታ ጎብኚዎችን አስተናግዷል። በዛሬው እለትም የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የስራ እድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ/ቤት አመራሮች፣ ሰራተኞች እና በክፍለ ከተማው በተለያዩ ዘርፎች የተደራጁ ማህበራት በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን ኤግዚቢሽን ጎብኝተዋል።

Share this Post