ታዳጊዎች ሀገራቸው እየሰራች ያለውን ቴክኖሎጂ በተግባር ማሳየት ተገቢ መሆኑን ገለፁ፡፡

ታዳጊዎች ሀገራቸው እየሰራች ያለውን ቴክኖሎጂ በተግባር ማሳየት ተገቢ መሆኑን ገለፁ፡፡ ከየካ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ሙድ ቤስት ቴኳንዶ ተማሪዎች በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን አውደርእይ በጎበኙበት ወቅት ታዳጊዎች ሀገራቸው እየሰራች ያለውን በተግባር ማሳየት ተገቢ መሆኑ ተገለጸ ፡፡ ነሀሴ 28/2015ዓም (ውኢሚ) "የውሃ ሀብታችን ለብልጽግናችን" በሚል የተዘጋጀውን ኤግዚብሽን ለመጎብኘት ታዳጊ ልጆችን ይዤ በመምጣቴ ተደስቼያለሁ ያሉት የሙድ ቤስት ቴኳንዶ ትምህርት ቤት ባለቤትና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሳቦም ከድር፤ ልጆች ከትምህርት ባሻገር እንደዚህ ያሉ ቦታዎችን እንዲያዩ ማድረግ ሀገራቸው እየሰራች ያለውን ነገር በተግባር ሲመለከቱ የነገ ተረካቢ ነኝ የሚል ስሜትን ያዳብራሉ፤ ይህም በቀጥታ ውሀና ኢነርጂ ከሀዳሴ ግድብ ውጪ የሌሎች ሰፋፊ ስራ ባለቤት መሆኑን ጭምር ያውቃሉ በማለት ገልጸዋል ፡፡ ኢንስትራክተሩ በማከል እንደሚታወቀዉ ሀገራችን የውሀ ጥራት ላይ ችግሮች ቢኖርም እዚህ በተግባር ያየሁት የውሀ ጥራት መለካትና ማከም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ደረጃ በማየቴ ተደስቻለሁ ብሏል፡፡ ሆኖም የውሀ ማጣሪያው ለእይታ ብቻ ሳይሆን ገበያ ለይ ቢኖርና ህብረተሰቡ ቢጠቀምበት በማለት አስተያየታቸውን አጋርተዋል፡፡ ከተማሪዎቹ ጋር አብረው ያገኘናቸው ወ/ሮ ሀና የተባሉ ወላጅ ዛሬ ከልጄ ጋር የመጣሁት ሀገሯን በተለይ ውሀና ኢነርጂን ከወሬ ባለፈ በተግባር እንድታይ ነው በማለት የገለፁ ሲሆን በተመሳሳይ ወ/ሮ ራውዳ ሀሰን የተባሉ ወላጅም ልጄ በአማራጭ ኢነርጂ ላይ ያሉትን ቴክኖሎጅ እንዲያውቅ ስለምፈልግ ነው አብሬ የመጣሁት ምክኒያቱም የባዮ ጋዝ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም የሞከርኩበት አጋጣሚ ስለነበር ይበልጥ እንዲረዳው በማሰብ ነው በማለት ገልጸው ሀገራችን ብዙ አማራጭ ኢነርጅ መጠቀም ስትችል በሀይል መቆራረጥ መፈጠሩ ለምሳሌ የሶላር ኢነርጂን ተደራሽ አለማድረግና የግንዛቤ እጥረት መኖሩን ያሳያል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ሀገራችን ሁልጊዜ የመስመር ሀይል ብቻ ሳይሆን ከተለያዩ ነገሮች ሀይል ማግኘት እንደሚቻል ልጄ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ታዳጊዎች ቢረዱ ና ቢያውቁ ለነገ መሰረት ይሆናቸዋል በማለት አስተያየት ሰጥተዋል ፡፡

Share this Post