በኤግዚቢሽኑ የቀረቡ ቴክኖሎጂዎች ዘርፉ የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳዩ ናቸው ተባለ።

በኤግዚቢሽኑ የቀረቡ ቴክኖሎጂዎች ዘርፉ የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳዩ ናቸው ተባለ። "የውሃ ሀብታችን ለብልፅግናችን!" በሚል መርህ የተዘጋጀው ሀገራዊ አውደርእይ ላይ ያነጋገርናቸው የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 8 ጎብኚዎች በራሳችን ባለሙያዎችና አነስተኛ ሶላርን በመጠቀም እስከ ግማሽ ሄክታር መሬት ማልማት የሚያስችል ሶላር የውሃ ፓምፕ በቴክኖሎጂ የታገዘውን የፈጠራ ስራ አድናቆት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል። ከግሪን ኢነርጂ ኃ.የተ.የግ.ማ ሲያስተዋውቁ ያገኘናቸው ባለሙያ በሰዓት 1,200 ሊትር በሶላር ኢነርጂ ፓምፕ የሚያደርገው የውሃ ፓምፕ ከ50 እስከ 60 ሜትር ጥልቀት ካለው የውሃ ጉድጓድ፣ ከሀይቅና ከወንዝ ፓምፕ በማድረግ ግማሽ ሄክታር መሬት ማልማት እንደሚችል ገልፀዋል። አያይዘውም ከቻይናና ከጀርመን የሚያስመጡትን እቃዎች በራሳቸው አቅም ገጣጥመው እስከ 70ሺ ብር የሚሸጡት የውሃ ፓምፕ ከ25 እስከ 30 አመት እንደሚያገለግል ገልፀው በሱማሌ ክልልና በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የመስመር መብራት በሌለበት አካባቢ1 ሺ ማህበረሰብ የመብራት ተጠቃሚ እንያደረገ እንደሆነ የገለፁት ባለሙያው ከ1 አምፖል ጀምሮ ለአካባቢ ነዋሪዎች ብሎም ጤና ጣቢያ፣ ትምህርት ቤትና ሆስፒታሎች አካባቢን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል። በሳይንስ ሙዚየም መሰል ቴክኖሎጅዎችን ይምጡና ይጎብኙ!

Share this Post