በውሃው ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና መሰጠቱ ለዘርፉ አቅም ግንባታ አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑ ተነገረ።

በውሃው ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና መሰጠቱ ለዘርፉ አቅም ግንባታ አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑ ተነገረ። ነሀሴ 15/2015 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) "የውሃ ሀብታችን ለብልፅግናችን" በሚል መርህ በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀው ሀገራዊ የውሃና የኢነርጂ ኤግዚቢሽን ላይ የተገኙ ጎብኝዎች በሰጡት አስተያየት በውሃው ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሙያዎች ተግባር ተኮር የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠቱ የዘርፍ ፉን ባለሙያዎች አቅም እንደሚያሳድግ ገልጸዋል ። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት በሀገር ደረጃ የተዘጋጀው ሀገር አቀፍ ኤግዚቢሽን በተቋሙ የሚሰሩ ስራዎችን ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅ ማህበረሰቡ ጋር ተደራሽ እንዲሆንና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋጥ በሚያስችል መልኩ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባው ተገልጿል። በኢንስቲትዩቱ "የግድቤን በደጀ'' ፕሮጀክት፤ በዝናብ ወቅት ውሃን በመያዝ ውሃ በሚያጥርበት ወቅት ዉሃን በማሰባሰብ ለመጠቀም የሚያስችልና ሶላር ፓምፕ፣ ፔዳል ፓምፕ እና ሌሎቾ ቴክኖሎጅዎች የሚተገበርበት፤ እንዲሁም ለውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ የሚያገለግሉ በሰውና በነዳጅ የሚሰሩ መሳሪያዎች ቀርበዋል። የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል በውሃው ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ሲሆን ስልጠናውን ከኬንያ፣ ከማላዊና ከናይጄሪ ለሚመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ሲሰጥ እንደነበር ተገልጿል። በጉብኝቱ ወቅት ያገኘናቸው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወጣቶች በሶላርና በሰው ሀይል የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ቴክኖሎጂዎች፣ የማሽነሪዎች ጥገና ፣ ከጉድጓድ እንዴት ውሃ ማውጣት እንደሚቻልና የዝናብ ውሃን እንዴት መያዝ እንደሚቻል መቅረቡ፤ ከሱዳን፣ ከማላዊና ከናይጄሪያ ለመጡ የውሃ ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱ በዘርፉ የአቅም ግንባታ ስራ የተሰጠውን ትኩረት ያሳያል ተብሏል። ወጣቶቹ ሌሎች ወጣቶች በሳይንስ ሙዚየም መጥተው ስለውሃና ኢነርጂ ጉዳዮች እንዲረዱ ጥሪ አቅርበዋል። "ይምጡና ይጎብኙ፤ እየተዝናኑ ይማራሉ!"

Share this Post