ግዙፉ የገልጨት-ሰሪቴ የውኃ አቅርቦት ፕሮጀክት የህብረተሰቡን ህይወት የሚቀይር ነው። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ

ግዙፉ የገልጨት-ሰሪቴ የውኃ አቅርቦት ፕሮጀክት የህብረተሰቡን ህይወት የሚቀይር ነው። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ግንቦት 19/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለህዝብ ያስተላለፉት መልዕክት እንደሚያመለክተው፣ በምሥራቅ ቦረና እና በቦረና ዞኖች የሚገኙ ነዋሪዎችን ህይወት የሚቀይር ግዙፍ የውኃ አቅርቦት ፕሮጀክት እየተገነባ ነው ብለዋል። አክለውም ይህ ፕሮጀክት ለህብረተሰቡ አስተማማኝ ንጹህ ውኃ ተደራሽ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወት መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም ፕሮጀክቱ በርካታ ኪሎ ሜትሮችን የሚዘልቁ የቧንቧ መስመሮች፣ ዘመናዊ የውኃ ማከፋፈያ ጣቢያዎች እንዲሁም ሰፋፊ የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ያካተተ ዘላቂ መሠረተ ልማት እየተገነባ መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክቱ ድርቅን ከመከላከል ባለፈ የሕዝብ ጤናን በማስጠበቅ፣ የነዋሪዎችን መተዳደሪያ አቅም በማጠናከር እና መጪው ትውልድ የሚጠቀምበትን የግብርና እምቅ አቅም በማዘጋጀት ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አመልክተዋል። ፕሮጀክቱ በቦረና ቀጣና የሚኖሩ ህብረተሰቦችን ቀጣይነት ያለው የንጹህ ውኃ ተደራሽነት ማረጋገጡንም ተጠቁሟል።

Share this Post