ለኢባላ-አዲሎ ከተማ ከመጠጥ ውሃ ግንባታ፣ የኤሌክትሮሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ፕሮጀክት ጋር የውል ስምምነት ተፈረመ።

ለኢባላ-አዲሎ ከተማ ከመጠጥ ውሃ ግንባታ ፣ የኤሌክትሮሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ፕሮጀክት ጋር የውል ስምምነት ተፈረመ። ሚያዚያ 13/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከምባታ ዞን ለምትገኘው ለኢባላ-አዲሎ ከተማ ከመጠጥ ውሃ ግንባታና የኤሌክትሮሜካኒካል አቅርቦትና ተከላ ፕሮጀክት ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ። የውል ስምምነቱን የፈረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ሲሆኑ ውል የተገባው ከተገኝ ተረፈ የግንባታና የውሃ ስራዎች ጠቅላላ ኮንትራክተር ጋር ነው። ለፕሮጀክቱ የተመደበው ጠቅላላ በጀት 93,521,734.05 ETB ሲሆን ወጪው በአፍሪካ የውሃ ፋሲሊቲ ፋይናንስ የሚደረግና በአፍሪካ ልማት ባንክ የሚሸፈን ሆኖ በውሉ መሰረት በ1ዓመት የሚጠናቀቅ ይሆናል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ተጠቃሚ የሚያደርገው የማህበረሰብ ቁጥርም 29,498 እንደሚሆን ተጠቅሷል። ከዚሁ ፕሮጀክት ጋር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከዚህ በፊት በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ከሚሰሩ ስራዎች ጋር በተገናኘ ሲሰራ መቆየቱን ክቡር አምባሳደዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ አስታውሰው ይህንኑም በ1ዓመት ጊዜ እንዲያጠናቅቅ ውል መገባቱን አመልክተዋል ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም የአካባቢውን ማህበረሰብ የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን የተናገሩት ክቡር አምባሳደሩ በአካባቢው ነዋሪና በዞን ደረጃም ቴክኒካል ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። ኮንትራክተሩ በበኩላቸው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሃሳብ በመስማማት ስራውን በሙሉ ሃላፊነት እንደሚወጡና ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀደም ብለው እንደሚያጠናቅቁ ቃል ገብተዋል።

Share this Post