በኔፕ-አዴሌ ፕሮጀክት ትግበራ መመሪያ እና በአካባቢ ጥበቃ አስተዳደር ስርአት ዙሪ ግንዛቤ መፍጠር የተሻለ አፈጻጸምን እንሚያመጣ ተገለጸ።
ታህሳስ18/2018 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የብሔራዊ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም አካል የሆነው የአዴሌ ፕሮጀክት (Access to Distributed Electricity and Lighting in Ethiopia (ADELE) Project) አተገባበር ዙሪያ በአዳማ ከተማ ስልጠና እየተሠጠ ነው።
የስልጠና መርሀግብሩን በንግግር ያስጀመሩት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ትግበራን ለማሳለጥ ፕሮጀክቱን ለሚተገብሩ እና ለባለድርሻ አካላት የተለያዩ ቴክኒካል እና የአቅም ግንባታን ስራዎችን በማከናወን የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራሙን ትግበራ ለማሳለጥ አቅምን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ሚኒስቴር ዲኤታው በማያያዝ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚተገበሩት ተግባራት አንዱ ለሆነው በጣም ገጠራማ ለሆኑ አከባቢዎች/Deep Rural areas/ በውጤት ተኮር የገንዘብ ድጎማ/Result Based Finance Grant/ የቤተሰብ ሶላር ሆም ሲስተም/Solar Home System/ በገጠር ላሉት የማህበረሰብ ክፍሎች ለማሰራጨት ቅድሚያ መዘጋጀት ባለቸው ሰነዶች ላይ ሰልጠና እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ በዋናነት እየተገበራቸው በሚገኙ አዲስ አበባን ጨምሮ ሰባት ከተሞች የኤሌክትሪክ መስመሮችን የመልሶ ማጠናከር፣ከዋናው መስመር ውጭ ለሚገኙ አካባቢዎች ሶላር ግሪድ መገንባት፣በጣም ገጠራማ ለሆኑ አካባቢዎች ሶላር ሆም ሲስተም ፣ ተቋማዊ ሶላር ሲስተምን እና ጥገናና ዝርጋ ሰራ ላይ በሚረዱ ሰነዶች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር የታሰበ ነው ብለዋል።
የፕሮጀክቱን የማስፈጸሚያ ማኑዋል (Specific Operational Manual) ላይ እና የአካባቢ እና ማህበራዊ ማኔጅመንት ስርዓት እና (Environmental and Social Management System) ተዘጋጅቶ በትግበራ ላይ እንደሚገኙና ፕሮጀክቱ በዋናነት በክልሎች የሚተገበር በመሆኑና በተዘጋጁት ሰነዶች ላይ ስልጠናን መስጠት አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል።
ለክልል ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊዎች፣ ለክልል፣ ለዞን እና ወረዳ ተወካዮችን በፕሮጀክቱ አተገባበር እና የአካባቢ የማህበረሰብ አስተዳደር ስርአት መመሪያ ዙሪያ ስልጠና መስጠት የተሻለ አፈጻጸም እንደሚያመጣ ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው ገልጸዋል።
በመጨረሻም የተዘጋጀውን ስልጠና በአግባቡ በመከታተል እየተተገበረ በሚገኘው የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም የድርሻችሁን ኃላፊነት በመውሰድ ከሚመለከታቸው የመንግስት ድርጅቶች በዋናነት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ከትምህርት ቢሮና ከጤና ቢሮ እንዲሁም ከግል ሶላር አከፋፋዮች እና አሰራጮች በጋራ በመሆን ስራዎችን በጥራትና በአግባቡ እንንዲተገበር ስልጠናው የሚያስገኘዉን ትልቅ ጥቅም በመረዳት፣ ተሳትፎ በማድረግ በኤሌክትሪፊኬሽን ዘርፍ የሚጠበቀው ውጤት እንዲመጣ የድርሻሁን እንድትወጡ አሳስባለሁ ብለዋል።
በስልጠናው የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ምክትል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ሀሰን በሀገራችን ትልቁ ዘርፍ ኢነርጂ መሆኑን ገልጸው በአማራጭ ኢነርጂ ላይ ውጤታማ ስራ እየሰራ ያለና በተለይ ከዋና መስመር ውጪ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ፕሮጀክቶች ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ እና የኤሌክትሪክ ተደራሽ ለማድረግ የሚኒ ግሪድ አሰራር ስርአት ዘርግቶ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
በዚህ ስራ ላይ ከውሃና ኢነርጂ ማኒስቴር ጋር በጋራ ፕሮጀክቱን ለመተግበር ሁሉም ባለሙያ በትብብር በመስራት ህብረተሰቡን የአማራጭ ኢነርጂ ተጠቃሚ ማድረግ አለብን በማለት አቶ ከድር አሳስበዋል ።
በስልጠናው ላይ ከክልሎች ከዞኖችና ከወረዳ የኢነርጂ ቢሮ ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው አካላት የተሳተፋ ሲሆን ስልጠናው ለቀጣይ ሁለት ቀን በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይም እንደሚሰጥ ተገልጿል።