የከርሰ-ምድር ውሃ ጥናት ዲዛይንና የጉድጓድ ቁፋሮ ቁጥጥር የውል ስምምነት ተፈረመ፡፡
ግንቦት 01/2017 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአፍርካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት ከ317.3 ሚሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጪ በአራት ክልሎች በ5 አካባበቢዎች የከርሰምድር ውሃ ጥናት፣ ዲዛንና የጉድጓድ ቁፋሮ ቁጥጥር ለማካሄድ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የውል ስምምነት አድርጓል፡፡
የውል ስምምነቱን በተፈረመበት ወቅት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ለከርሰምድር ውሃ ስራ የጥናት ምዕራፍ ዋነኛውና መሰረታዊ ጉዳይ በመሆኑ በከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ በመተግበር በታቀደው ጊዜ፣ በጥራትና በፍጥነት እንዲጠናቀቅ አሳስበዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም ለስራው ፍጥነትና ጥራት የተቋማችን የሚመለከታቸው ባለሙያዎች፣ አማካሪዎችና አመራሮች በቅንጅትና በትብብር አብሮ ለመስራት ዝግጁ ናቸው ብለዋል፡፡
የከርሰ ምድር ውሃ ጥናት ዲዛይንና የጉድጓድ ቁፋሮ ቁጥጥር የሚተገበረው በ4 ክልሎች ሲሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አባያ ጫሞ አካባቢ፣ በደቡብ ምዕራብ ክልል ግምቦ ጨና አካባቢ፣ በአፋር ክልል ገዋኔ አዳይቱ አካባቢና በአማራ ክልል አጣዬ ሽዋ ሮቢት አካባበቢ እንደሆነ ተገልጿል፡፡