በኔፕ-አዴሌ ፕሮጀክት ትግበራ መመሪያ እና በአካባቢ ጥበቃ አስተዳደር ስርአት ዙሪያ ለባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡
መጋቢት 25/2017 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የብሔራዊ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም አካል የሆነው የአዴሌ ፕሮጀክት (Access to Distributed Electricity and Lighting in Ethiopia (ADELE) Project) አተገባበር ዙሪያ ከክልልች እና ዞኖች ለተወጣጡ ባለሙያዎች ስልጠና በጅማ መሰጠት ተጀመረ።
የስልጠና መርሀግብሩን በንግግር ያስጀመሩት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ትግበራን ለማሳለጥ ፕሮጀክቱን ለሚተገብሩ እና ለባለድርሻ አካላት የተለያዩ ቴክኒካል እና የአቅም ግንባታን ስራዎችን በማከናወን የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራሙን ትግበራ ለማሳለጥ አቅምን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን አንስተው፤ ስልጠና የዚሁ አካል መሆኑን ገልጸዋል።
ሚኒስቴር ዲኤታው በማያያዝ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚተገበሩት ተግባራት አንዱ ለሆነው በጣም ገጠራማ ለሆኑ አከባቢዎች/Deep Rural areas/ በውጤት ተኮር የገንዘብ ድጎማ/Result Based Finance Grant/ የቤተሰብ ሶላር ሆም ሲስተም/Solar Home System/ በገጠር ላሉት የማህበረሰብ ክፍሎች ለማሰራጨት ቅድሚያ መዘጋጀት ካለባቸው ሰነዶች ውስጥ የፕሮጀክቱን የማስፈጸሚያ ማኑዋል (Specific Operational Manual) ላይ እና የአካባቢ እና ማህበራዊ ማኔጅመንት ስርዓት እና (Environmental and Social Management System) ተዘጋጅቶ በትግበራ ላይ እንደሚገኙና ፕሮጀክቱ በዋናነት በክልሎች የሚተገበር በመሆኑና በተዘጋጁት ሰነዶች ላይ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን አውስተው፤ ከአሁን በፊት በፕሮጀክቱ መመርያ ትግበራ እና ESMS ሰነድ ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና የተሰጠና አሁኑ ላይ ደግሞ ለክልል ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊዎች፣ ለክልል፣ ለዞን እና ወረዳ ተወካዮችን በፕሮጀክቱ አተገባበር እና የአካባቢ እና የማህበረሰብ አስተዳደር ስርአት መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ለሁሉም ክልሎች ለመስጠት መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በማያያዝ በዚህ ስልጠና ስለ ብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም፣ Ethiopian Electrification program (ELEAP) እና አደሌ ፕሮጀክት አጠቃላይ ግንዛቤ
ለክልሎችና ለባለድሻ አካላት ማስጨበጥና በተለየ መልኩ ደግሞ ለኮምፖነንት 3 (component 3) ሶላር ሆም ሲስተም የተዘጋጀውን የአካባቢና ማሕበራዊ አስተዳደር መተግበሪያ (ESMS) ሰነድ ላይ ሰፊ ትኩረት በማድረግ ስልጠናው ይሰጣል ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በመጨረሻም የተዘጋጀውን ስልጠና በአግባቡ በመከታተል፣ የስራ ድርሻችሁን አውቃችሁ እየተተገበረ በሚገኘው የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም የድርሻችሁ ኃላፊነት በመውሰድ ከሚመለከታቸው የመንግስት ድርጅቶች በዋናነት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ከትምህርት ቢሮና ከጤና ቢሮ እንዲሁም ከግል ሶላር አከፋፋዮች እና አሰራጮች በጋራ በመሆን ስራዎችን በጥራትና በአግባቡ እንድንተገብር ስልጠናው የሚያስገኘዉን ትልቅ ጥቅም በመረዳት፣ ተሳትፎ በማድረግ፣ መልካም ልምዶችን በመጋራትና ወደ መጣንበት ስንመለስ በስራችን ያሉትን በማሰልጠንና በማብቃት እንዲሁም፤ ስለ ፕሮጀክቱ ግንዛቤ በመስጠት በኤሌክትሪፊኬሽን ዘርፍ የሚጠበቀው ውጤት እንዲመጣ የድርሻሁን እንድትወጡ አሳስባለሁ ብለዋል።
በስልጠናው ላይ ከክልሎች ከዞኖችና ከወረዳ የኢነርጂ ቢሮ ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው አካላት የተሳተፋ ሲሆን ስልጠናው ለቀጣይ ሁለት ቀን በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይም እንደሚሰጥ ተገልጿል።