በባቱ ደምበል ሐይቅ አካባቢ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ተካሄደ፡፡

የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ከስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ተፋሰስ ልማት ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ጋር በመሆን በባቱ ደምበል ሐይቅ አካባቢ የችግኝ ተከላ አካሄዱ::

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ተፋሰስ ልማት ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ጋር በመሆን በባቱ ደምበል ሐይቅ አካባቢ ችግኝ ተካላ አካሄዱ፡፡ በችግኝ ተከላው ላይ የተገኙት ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር የተተከሉ ችግኞች እንደ ሕጻናት ትኩረትና እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ገልጸው በችግኝ ተከላው ላይ የተሳተፉና የአካባቢው ነዋሪዎች የተተከሉትን ችግኞች እንዲንከባከቡ ጠይቀዋል፤ በተከላው ላይ ለተሳተፉም ምስጋና አቀርበዋል፡፡

ከችግኝ ተከላው በኋላ በደንበል ሐይቅ/ዝዋይ ሐይቅ ተከስቶ የነበረውን የእንቦጭ አረም በማስወገድ ረገድ የተሠራው ሥራ የአፈጻጸም ሪፖርትና የ2015 ዓ.ም ዕቅድ በቅደም ተከተል በስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ተፋሰስ ልማት ጽ/ቤት የዝዋይ ቅርንጫፍ ኃላፊ አቶ ጀማል ሁሴንና በስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ተፋሰስ ልማት ጽ/ቤት የአካባቢ ባለሙያ አቶ ገረመው ገብሩ ቀርቧል፡፡ በአፈጻጸሙም ወቅት ለተሳተፉት ተቋማትና ድርጅቶች እንዲሁም ለባቱ ከተማ አስተዳደር የዕውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷል፡፡ በአፈጻጸም ወቅት ላሳዩት ትጋትና ላስመዘገቡት ውጤት፣ወደፊትም ሥራውን በስፋት እንዲያስተባብሩና እንዲመሩ ለባቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የሞተር ሳይክል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በመጨረሻም በክቡር ሚኒስትሩ የሥራ አቅጣጫ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል፡፡ ዘገባው የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ተፋሰስ ጽ/ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ነው፡፡

Share this Post