ተደጋግሞ ሊታይ የሚገባው አውደ ርዕይ ነው። ----- ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለ

ተደጋግሞ ሊታይ የሚገባው አውደ ርዕይ ነው። ------------------------- ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ም/ኃላፊ መስከረም 8/2016ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) ሊጠናቀቅ ሁለት ቀናት ብቻ የቀረውን የውሃና ኢነርጂ አውደርዕይ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ጎብኝተዋል። ከጉብኝት በኋላ የጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊው ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለ የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር በየዘርፉ እየሰራቸው ያሉትን ስራዎች ለወጣቶች፣ለተማሪዎች እንዲሁም ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አስተማሪ በሆነ መንገድ ተዘጋጅቶ የቀረበ አውደርዕይ ሲሉ ገልጸውታል። የውሃ ሀብታችን ምን ያህል እንደሆነ፣በተለያየ መንገድ ለአገልግሎት እንዴት እንደሚውል፣ጥራቱ እንዴት እንደሚጠበቅ እንዲሁም አጠቃቀማችን ምን እንደሚመስል ጭምር ትምህርት የሚሰጥ ነውም ብለዋል። አክለውም ውሃ ከመጠጥነት ባለፈ ለኢነርጂ ምንጭ እና ሌሎች አገልግሎቶች እንዴት እንደሚውል የሚያስገነዝብ እንዲሁም ህዳሴ ግድብ ለዕይታ የቀረበበት መንገድ እያዝናና እውቀት የሚያስጨብጥ ሆኖ አግኝቸዋለሁ ብለዋል። ተቋሙ ለሌሎች ሴክተሮችም የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ቀላል የሚባል አይደለም የሚሉት ም/ቢሮ ኃላፊዉ በዘርፉ ልናውቃቸው የሚገቡ ትክኖሎጅዎች ተደጋግመው መታየት የሚገባቸው ናቸው ሲሉ ባዩት ነገር መገረማቸውን ገልጸዋል። በእለቱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚው አቶ ጌትነት ጌጡ ለጎብኝዎች እየተዝናኑ ቴክኖሎጅዎችን እንደሚተዋወቁ እና ጠቃሚ መረጃ እንደሚያገኙ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

Share this Post