የአንድ ቋት ብሔራዊ ዋሽ ፕሮግራም Phase II የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ስኬታማ መሆኑ ተገለጸ።

የአንድ ቋት ብሔራዊ ዋሽ ፕሮግራም Phase II የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ስኬታማ መሆኑ ተገለጸ።

አዳማ ጥቅምት 3/2019 ዓም (ው.ኢ.ሚ) የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ፌዝ የስድስት ወር አፈጻጸምን በተመለከተ ባደረጉት ምልከታ ከባፈው የተሸለ ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡ ተገልጿል ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ታምሩ ገደፋ በየስድስት ወሩ በአምስት ቡድን የተውጣጡ አካላት ከሁሉም ክልሎች ዳሰሳ በማድረግ ማጠቃለያ ሪፓርት ያቀረቡ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አቶ ታምሩ በማከል በቀረቡ ሪፖርት መደሰታቸውን ገልጸው የተመዘገበው ውጤት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራርና ባለሙያ የCWA II የትግበራ ሂደትን እና ሰፊውን የOWNP ግምገማ፣ቁልፍ ስኬቶችን፣ ተግዳሮቶችን እና የተማሩትን ትምህርቶች መለየት፣በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ ክልሎች እና አጋሮች መካከል በቅንጅትን በመስራታቸው የተገኘ ውጤት ነውም ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የአንድ ቋት ብሄራዊ ዋሽ ፕሮግራም የሁለተኛው ፌዝ የስድስት ወር አፈጻጸምን በተመለከተ ያደረጉትን ምልከታ ሪፖርት ለሚመለከታቸው አካላት ያቀረቡ ሲሆን እየተተገበሩ ያሉ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ከባለፈው የተሻለ ጥሩ አፈጻጸም ላይ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይ ከዚህ በበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባል በማለት አቶ ታምሩ አሳስበዋል ።

የብሔራዊ ዋን ዋሽ አስተባባሪ አቶ አብይ ግርማ ከዚህ በፊት ከፌደራል ጀምሮ ያሉ ሴክተሮች ያለውን የስራ አፈጻጸም ወደ መስክ በመውረድ በመገምግም ወደ ኋላ የቀሩትን ችግሮች በመለየትና በመፍታት፣ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ፕሮግራሙ በተያዘለት ጊዜ እንዲያልቅ እየተሰራ መሆኑን አውስተው፤ባለፈው ስድሰት ወር ጥሩ ውጤት የታየበትና ብዙ ፕሮጀክቶች ውል ተገብቶላቸው ወደ ስራ በመግባት ጥሩ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጸዋል ፡፡

አቶ አብይ ስራው ከውሃ፣ ከጤና፣ ከትምህርት፣ ከፋይናንስ እንዲሁም ፕሮግራሙን ከሚደግፉ አጋር ድርጅቶች፤ አለም ባንክ፣ የእንግሊዝ መንግስት፣ ዩኒሴፍ ጋር በመሆን ግባችን ያለፈውን አፈፃፀም መገምገም ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱ መንገዱን በማጽዳት የስርዓት ማነቆዎች በመፍታት የCWA IIን ስኬት በማረጋገጥ ወደ ሚቀጥለው የፕሮግራሙ ምዕራፍ ለመቀጠል የሚያስችል ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ ከጤና፣ ከትምህር ፣ከፋይናስና ከውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ CWA II የልማት አጋሮች እና የዋሽ ዘርፍ የተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈውበታል፡፡

Share this Post