የቤዚን አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶችን የዲጂታል አሠራር ለማጠናከር የMicrosoft 365 አቅም ግንባታ ሥልጠና ተጀመረ።
የቤዚን አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶችን የዲጂታል አሠራር ለማጠናከር የMicrosoft 365 አቅም ግንባታ ሥልጠና ተጀመረ።
አዲስ አበባ : ጥቅምት 21/2019ዓ.ም
የቤዚን አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶችን የሥራ ቅልጥፍና፣ የመረጃ ልውውጥና ተቋማዊ ትብብር ለማሳደግ ያለመ የMicrosoft 365 እና የOutlook Web App (OWA) አጠቃቀም አቅም ግንባታ ሥልጠና ተጀመረ።
ሥልጠናውን በይፋ የከፈቱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የቤዚን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደጀኔ ለገሠ፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ መጠቀም የተቋሙን አቅም ለማሳደግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማፋጠንና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደትን ለማሻሻል ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የሥልጠናው ዋና ዓላማ የቤዚን አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች የማኔጅመንት አባላትና አመራሮች የሚኒስቴሩን ይፋዊ የኢሜይል ሥርዓትና የMicrosoft 365 መሣሪያዎችን በተግባር በመጠቀም የዕለት ተዕለት ሥራዎቻቸውን በተቀላጠፈና በዘመናዊ መንገድ እንዲያከናውኑ ማስቻል ነው።
በሥልጠናው የኢሜይል፣ የቀን መቁጠሪያ፣ የዕውቂያና የስብሰባ አስተዳደርን ማዘመን፣ OneDrive፣ Microsoft Teams፣ Word እና Excel የመሳሰሉ የMicrosoft 365 መሣሪያዎችን ለተቋማዊ ሥራዎች በብቃት መጠቀም እንዲሁም ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ልውውጥን ማጠናከር ላይ ትኩረት ይደረጋል።
ከዚህም በተጨማሪ ወረቀት አልባ አሠራርን በማስፋፋት የጊዜና የወጪ ቁጠባን ማሳደግ፣ የሥራ መረጃዎችን ደህንነታቸው ተጠብቆ ከተለያዩ ቦታዎች ማግኘትና ማጋራት እንዲሁም የሥራ ትብብርን ማጠናከር ከሥልጠናው የሚጠበቁ ውጤቶች ናቸው ብለዋል።
አቶ ደጀኔ የዲጂታል ሪፎርሙ ስኬት ከከፍተኛ አመራሩና ከማኔጅመንት አባላት አርአያነት እንደሚጀምር ጠቁመው፣ የሥልጠናው ተሳታፊዎች በተግባራዊ ልምምዶችና በቡድን ውይይቶች በንቃት በመሳተፍ ያገኙትን እውቀት በዕለት ተዕለት ሥራቸው ላይ እንዲተገብሩ አሳስበዋል።
በአጠቃላይ፣ ሥልጠናው በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተጀመረውን የዲጂታል ሽግግር ሂደት በማጠናከር፣ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የሥራ ባህል ለመገንባት አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።